ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረው የሞንጎምሪ ካውንቲ አረንጓዴ ፈስቲቫል ነገ ቅዳሜ ኤፕሪል 23 ከ11am-5pm ዊተን በሚገኘው ብሩክሳይድ ጋርደን ይከበራል።
በፌስቲቫሉ ላይ ከ60 በላይ ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁ ሲሆን የኤሌትሪክ መኪና ትርዒትም ይኖራል ተብሏል። በተጨማሪም ለልጆች የታቀዱ መዝናኛዎች፣ የዛፍ መንጠላጠያዎች፤ የልጆች ዮጋ፤ ፌስ ፔይንቲንግ እና የተለያዩ አትክልቶች በነፃ ይታደላሉ። በተጨማሪም ጎብኚዎች በፌስቲቫሉ ላይ የሚቀርቡትን የስነጥበብ ስራዎች መገብየት ይችላሉ። የኤሌትሪክ መኪና ትርዒቱ ላይ ዘመናዊ መኪኖችና በዓለም የመጀመሪያው የኤሌትሪክ የጭነት መኪና (ትራክ) የሆነው Rivian ለዕይታ ይቀርባል።
ጎብኚዎች የመኪና ማቆሚያ እንዳይቸገሩ መኪናቸውን በነፃ ግሌንሞንት ሜትሮ ስቴሽን አቁመው ወደብሩክሳይድ ጋርደን በየ15 ደቂቃው በነጻ ታዳሚዎችን የሚያመላልሱ የሸትል ባስ አገልግሎት ከጠዋቱ 10፡30 ጀምሮ ተዘጋጅቷል። የቤት እንስሳ (Pets) ይዞ መምጣት አይቻልም። ለበለጠ መረጃ ይቺን ተጭነው ይሂዱ።