6660dcdfc18be5245ee0bc5f_Plunkert-ethiopia-b

ኢን-ሲሪየስ የተባለው የስነጥበብ ተቋም ለረጅም ጊዜ በአሜሪካ መንግስት በተለይም የጥበብ ስራው በተዘጋጀበት ወቅት በ1930ዎቹ ፕሬዘደንት በነበሩት ቴዎዶር ሩዝቬልት አስተዳደር እንዳይታይና ለህዝብ ይፋ እንዳይሆን ተከልክሎ የቆየውንና ስለ ሁለተኛው የጣሊያን ወረራ የሚያትተውንና “ኢትዮጵያ” የተባለውን ቲያትር በዲሲና በባልቲሞር ከሜይ 16 ጀምሮ ለህዝብ ሊያሳይ እንደሆነ ተነግሯል።

በ1930ዎቹ በነበረው የኢኮኖሚ መውደቅ ምክንያት በሩዝቬልት የሚመራው የአሜሪካ ፌደራል መንግስት የጥበብ ሰዎች ስራ እንዳያጡ በማሰብ ትልቅ የትያትርና ሌሎች ጥበቦችን ያካተተና “ሊቪንግ ኒውስፔፐር” የተባለ ፕሮጀክት ነበረው።

ይህ ኢትዮጵያ የተባለ ስራም በ1937 በዚህ ፕሮጀክት ስር አርተር አርንት በተባለ የስነጥበብ ባለሞያ የተዘጋጀ ነበር።

ኢን-ሲሪየስ ታዲያ ከጥበብ ባለሞያዋና በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ አሜሪካውያንና የአፍሪካ ዲያስፖራ ጥናት ክፍል ሀላፊና መምህር ከሆኑት ሲቢል ሮበርትስጋ በመሆን ይህን የጥበብ ስራ ከተቀበረበት አውጥተው ይፋ አድርገውታል።

ኢትዮጲክ ያነጋገረቻቸው እኚህ ባለሞያ ታዲያ ይህ ለዘመናት ተደብቆ የቆየ የጥበብ ስራ በሶስት ወሳኝ ጉዳዮች ላይ አዲስ ግኝትን እንደሚያሳይ ተናግረዋል። ከነዚህም አንዱ የሁለተኛው የኢትዮ-ጣልያን ወረራ የፋሽስት በአለም መስፋፋትና የሁለተኛው የአለም ጦርነት መነሻ እንደነበረ የተገነዘብንበት እንደሆነ በሁለተኛ ደረጃ ደሞ የጥቁር አሜሪካውንያን በኢትዮ-ኢጣልያ ጦርነት ወቅት ቀላል የማይባል የአክቲቪዝም (ማስተባበርና የድጋፍ) ሚና እንደነበራቸውና በሶስተኛ ደረጃ የአንድ አፍሪካ (ፓን አፍሪካ) አቀንቃኞች በዛን ወቅትም ከጥቁር አሜሪካውያንና ከኢትዮጵያውያን ወገኖች እንደነበሩ ተናግረዋል።

ይህ ቲያትር በዋናነት በቺካጎ የኢትዮጵያ ወርልድ ፌዴሬሽን መስራጭ በሆነችው ማይሚ ሪቻርድሰን ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ እንደሆነና በወቅቱ የጥቁር አሜሪካውያን ድጋፍ ለኢትዮጵያ ምን ያህል እንደነበርና የኢምፔሪያሊዝምን የጭቆና ታሪክ ለሁሉም ማስገንዘብና ሰው ሰራሽ ክፍፍሎችን እንደሚያሳይ ፀሐፌ-ተውኔቷ ተናግረዋል።

ኢትዮጲክ ያነጋገረቻቸው የዚህ ቲያትር ዳይሬክተር ቲመቲ ኔልሰን በበኩላቸው ይህ በዚህ ቲያትር ያልተነገሩ ተረኮችን ለመዘከር እንደሚያስቡና የተደበቁ ታሪኮችን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርጉ በተለይም የጥቁር አሜሪካውያን በአለም ፖለቲካና በፓን አፍሪካኒዝም ጉዳዮች ላይ የነበራቸውን የነቃ ተሳትፎ እንደሚያሳዩበትና ለጭቁን አፍሪካውያን ድምጽ እንደነበሩ እንደሚታይበት አውስተዋል።

የሙዚቃ ዳይሬክተሯ ጀኔል ጊል በበኩላቸው ሙዚቃዊ የታሪክ ትርክት ዘይቤን ተከትለው በተለይም እንደ እማሆይ ጽጌማርያም አይነት ሙዚቃዊ አቀራረብ ባለው መልኩ ለዚህ ቲያትር ይመጥናል ያሉትን ሙዚቃ እንዳዘጋጁና በዚህ ስራቸውም የማህበረሰቦችን ጥንካሬ፤ ጽናት፤ ተስፋ እንዲሁም በጥቁር አሜሪካውያንና በኢትዮጵያውያን ዘንድ የነበረውን ተመሳሳይ ትግል ለማሳየት እንደሚጥሩ ተናግረዋል።

ይህ ታሪካዊ ቲያትር ሜይ 16 ምሽት 7፡30pm በ340 MAPLE DR – DC WATERFRONT/WHARF የሚጀምር ሲሆን በተከታታይ ሜይ 17 ና ሜይ 18ም በዲሲ ይከናወናል።
በባልቲሞር የቲያትር ፕሮጀክት ውስጥ ደግሞ ከሜይ 30 እስከ ጁን 1 ድረስ እንደሚከናወን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል። ቲኬቶቹን ገዝቶ ለመታደም የሚፈልግ ማንናውም ሰው ሊንኩን በመጫን መግዛት ይችላል

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.