@ethiopique202 (69)

በሜሪላንድ በቅርቡ የተደረገ ኦዲት ከ2003 እስከ 2019 ባለው ጊዜ ውስጥ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያሉ ለህልፈት የተዳረጉ 36 ሰዎች የህልፈት ሪፖርት በተሳሳተ መንገድ እንደተመደበ እና በፖሊስ ተገለው እያለ በተፈጥሯዊ መንገድ ሞተዋል ተብሎ ሪፖርት እንደተደረገ ተነግሯል።

ሐሙስ ሜይ 15 ቀን 2025 ይፋ የሆነው ይህ ሪፖርት እ.ኤ.አ. በ2021 በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ወቅት የአስከሬን መርማሪ የነበሩትና ከዛ በፊት ደሞ የሜሪላንድ ዋና አስከሬን መርማሪ የነበሩት ዶክተር ዴቪድ ፋውለር በሰጡት ምስክርነት ጆርጅ ፍሎይድ ለህልፈት የተዳረገው ከዚህ ቀደም በነበረበት የልብ ጤና እክል ነው እንጂ በፖሊስ ምክንያት አይደለም የሚል ሪፖርት ይፋ ካደረጉ በኋላ በርካታ በዘርፉ ያሉ ባለሞያዎች ተቃውሞ አሰምተው ነበር።

ትላንት ይፋ የሆነው የኦዲት ሪፖርት ከፖሊስ ጋር በተያያዙ ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች በተለይም የዘር መድልዎ ሊያጋጥም እንደሚችልና ከህልፈት በኋላ የሚኖረው የአስከሬን ምርመራ ውጤት አጠያያቂ እንደሆነና በአሰራር ላይ ከባድ የኢ-ፍትኃዊነት ችግሮች እንዳሉ አመልክቷል።


በሜሪላንድ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አንቶኒ ብራውን የሚመራው ግምገማ በፖሊስ ከተያዙ በኋላ ለህልፈት የተዳረጉ 87 ሰዎችን ጉዳይ የመረመረ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ታዲያ በገለልተኛ ወገን ምርመራ ውጤቱ 36ቱ በፖሊስ ለህልፈት እንደተዳረጉ መመዝገብ ሲገባቸው እንደ አደጋ፤ ተፈጥሯዊ ህልፈት ወይንም ምንነቱ ባልታወቀ በሚሉ በርካታ ምክንያቶች እንደሞቱ ተደርገው ፋይላቸው እተዘግቷል። በዚህ ሪፖርት እንደታየውም በዚህ አይነት ግድፈት የሚጠቁት በአብዛኛው ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች እንደሆኑ ተነግሯል።


ለዚህ ምርመራ እንደ መነሻ የሆነውና ጥርጣሬን ያጫረው በበርካታ ሪፖርቶች ላይ የሞቱት ሰዎች ለህልፈታቸው ምክንያት ከባድ መደናገጥና መነቃቃት ወይንም የአይምሮ መዛባት (excited delirium) እንደ አንድ ትልቅ ችግርና የሞት ምክንያት ሆኖ ጥቅም ላይ መዋሉ ነው። በአሁኑ ጊዜ በሰፊው ያልተረጋገጠው ይህ ቃል የፖሊስን ድርጊት ከመውቀስ ይልቅ ሞትን ለማስረዳት ሟችን ጥፋተኛ ለማድረግ ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ውሏል። ኦዲቱ ይህንን ቃል ከዚህ በኋላ መጠቀምን እንዲታገድ ይመክራል።
በዚህ መልኩ ለህልፈት ከተዳረጉት መሀል ታዋቂ የነበረውና በ2018 በፖሊስ ከታሰረ በኋላ የሞተው የ19 ዓመቱ ጥቁር ታዳጊ አንቷን ብላክ እና በ2013 ከባልቲሞር ፖሊስ መኮንኖች ጋር ከተጋጨ በኋላ የሞተው ታይሮን ዌስት ይገኙበታል። የሁለቱም ህልፈት ላይ የፖሊስ እጅ እንደነበረበት በማስረጃ ቢረጋገጥም በተሳሳተ መንገድ በሪፖርት ላይ ተመድበዋል።
የዚህ ሪፖርት ውጤትን ተከትሎ በዚህ ተግባር የተሳተፉ ፖሊሶች ላይ ክስና የመሳሰሉት ህጋዊ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ማለት ባይሆንም ገቨርነር ዌስ ሙር እነዚህን 41 ጉዳዮችን የሚገመግም እና ማንኛቸውም እንደገና መከፈት ያለባቸውን ኬዞች የሚወስን የሥራ ቡድን አዘዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.