@ethiopique202 (70)

ዛሬ ሜይ 16 ቀን 2025 በዋለው ችሎት የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 7-ለ2 በሆነ ድምፅ የትራምፕ አስተዳደር እ.ኤ.አ. በ1798 የወጣውን የሰርጎ ገብ ጠላቶች ህግን (Alien Enemies Act) በመጠቀም የቬንዙዌላ ስደተኞችን ለማባረር ያደረገውን ሙከራ አገደ። ለዚህም ምክንያት የተባለው ደሞ ስደተኞቹ ጉዳያቸውን ለሚመለከታቸው አካላት የሚያሰሙበት በቂ ጊዜና ሁኔታ አልተመቻቸላቸውም (Due Process) በሚል ነው።
ከዳኞች መሀከልም ወግ አጥባቂዎቹ ዳኞች ክላረንስ ቶማስ እና ሳሙኤል አሊቶ የትራምፕ አስተዳደርን በዚህ ጉዳይ ላይ ተቃውመዋል ።


ይህ ውሳኔ በሰሜን ቴክሳስ ብሉ ቦኔት የስደተኞች ማቆያ የታሰሩ እና የትሬን ደ አራጓ የወንበዴ ቡድን አባላት ናቸው ተብለው የተከሰሱ የቬንዙዌላ ስደተኞችን ለጊዜው ከማባረር ያቆመ ሲሆን ምክንያቱ ደሞ ለማባረር የቀረበባቸውን ክስ ለመቃወም የተሰጣቸው ጊዜ 24 ሰዓት ያህል ብቻ በመሆኑ ነበር።
ፍርድ ቤቱ ይህ የ24 ሰዓት ጊዜ ለስደተኞቹ ጉዳያቸውን ለማስረዳት በቂ የመዘጋጃ ጊዜ እንዳልሆነ በመግለጽ ስደተኞቹ ጉዳያቸውን እንዲያስረዱ የተቀመጠውን የህገ-መንግስት ትዕዛዝ (habeas corpus) ለማቅረብ በቂ ጊዜ ሊኖራቸው እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥቷል፣ ይህም የህግ የበላይነትን ያረጋግጣል ተብሏል።

በጽንፈኛው ግራ ዘመም ቡድኖች መጫወቻ እንደሆነና ይህ ቡድን ምንም የህዝብ ድጋፍ የሌለውና ፍርድ ቤቶቹን በማስፈራራት ውሳኔዎችን እንደሚያስቀለብስ ጠቁመዋል።

ፕሬዘደንቱ በሌላ ፖስት አክለውም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ወንጀለኞችን ከአገር እንዳናባርር አልፈቀደልንም ብለው ለጥፈዋል።

ከሰሞኑ እንደዘገብነው የፕሬዘደንቱ አማካሪ የሆኑት ስቴፈን ሚለር ስደተኞች ሀቢየስ ኮርፐስ በሚለው በፍርድ ቤት ቀርቦ ጉዳይን የማስረዳት መብት አይገባቸውም ሲሉ ተደምጠው የነበረ ሲሆን ይህ ውሳኔም ይህን ሀሳባቸውን የሚያደናቅፍ ውሳኔ እንደሆነም ባለሞያዎች ተናግረዋል። ለስደተኞችም እፎይታ ይሆናል ተብሏል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.