
በሜሪላንድ የሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ ዛሬ ዕሁድ ሜይ 18 ማምሻውን ባወጣው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ የ77 አመት አዛውንት የሆኑትን ወይዘሮ አስናቀች አምደሩፋዔል ነገዎን አፋልጉኝ ብሏል።
ወይዘሮ አስናቀች ቁመታቸው 5 ጫማ ከ4 ኢንች ሲሆን 165 ሲሆን ክብደታቸው 165 ፓውንድ ነው ተብሏል። ወይዘሮ አስናቀች ቡናማ የአይን ቀለም ሲኖረው ጸጉራቸው ደሞ ሸብቶ ግራጫማ ነው ሲል መግለጫው አክሎ አሳውቋል።
ወይዘሮ አስናቀች ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት እሁድ ሜይ 18 ከሰዓት 5፡30pm አካባቢ ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው በ13700 Avonshire Drive አቅራቢያ ነው ተብሏል።
ወይዘሮ አስናቀች በወቅቱ ጥቁር ሱሪ፤ ጥቁር ሰሚዝና ጥቁር ቦርሳ ይዘው ነበር ተብሏል።
ወይዘሮ አስናቀች ያሉበትን የሚያውቅ ወይንም ያያቸው ሰው ታዲያ በማንኛውም ሰዓት በስልክ ቁጥር (301) 279-8000 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ፖሊስ ጠይቋል።
