12/12/2024
272808258_124380260102145_2485873484865754143_n
ቆይታ ከኢትዮጲክጋ

ራስዎን አስተዋውቁልን
ሮበርት ዋይት እባላለሁ፡፡ ትውልድና እድገቴ እዚሁ ዋሽንግተን ዲሲ ሲሆን ባለትዳርና አባት ነኝ። ለከተማዬ ከንቲባነት የመወዳደሬ ምክንያት በዋናነት ችግሮቻችንን የሚፈታ፤ ማህበረሰቡን የሚሰማ፤ የነዋሪዎችን የለት ተለት ችግር የሚያዳምጥ መሪ ያስፈልገናል ብዬ ስለማምን ነው። በመንግስት ስራ ላይ ባሳለፍኳቸው 15 ዓመታት በሙሉ የሰዎችን ችግር ለመፍታት ጠንክሬ ስሰራ ቆይቻለሁ። በዚህም ጉዞዬ ምን መደረግ እንዳለበት ጠንቅቄ እረዳለሁ። በተጨማሪም የራሴ ቤተሰብ ያለበትን የኑሮ ፈተናና ትግል ስመለከት ነዋሪዎች ያለባቸውን የደህንነት ስጋት፤ የተሻለ ትምህርት ፍላጎትና ኑሮን አሸንፈው በከተማችን መኖር እንዲችሉ አስቸኳይ ስራ መሰራት አለበት ብዬ አምናለሁ።

በከንቲባነት ለመወዳደር ምን አነሳሳዎ?
ለከንቲባነት የምወዳደረው የከተማችንን የማደግ/የመሻሻል አቅም ስለማውቅ ነው። ከተማችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ገንዘብ አለው፡፡ ነዋሪዎች ይህን አቅም ይዘን ከተለመደው አሰራር የተለየ ነገር እንድንሰራ ይፈልጋሉ። ችግሮቻቸውን እንድንፈታላቸው ይሻሉ። ከዚህ አንፃር ታዲያ ይህ ጊዜ በጣም ወሳኝ ጊዜ ነው። ችግሮቻችንን መፍታት የሚያስችለን ገንዘቡ አለን ሆኖም ወደትግባር ለመቀየር ወሳኝና ራዕይ ያለው አመራር ያስፈልጋል። እኔም በተቻለኝ ሁሉ ከተማችንን ወደሚቀጥለው እርከን አሻግራታለሁ።
የጁን 21 ምርጫ ከኖቨምበሩ በምን ይለያል?
ነዋሪዎች ጁን 21 በሚደረገው የዴሞክራት ፕራይመሪ መሳተፍ ይኖርባቸዋል ምርጫውም ወሳኝ ነው። አብዛኛው የዲሲ ነዋሪ ዴሞክራት ነው፤፤ በሰኔ 21 የሚደረገው ምርጫ የከተማዋን ከንቲባ ማንነት ይወስናል። ስለሆነም በሰኔው ምርጫ ወይ የተለመደውን አሮጌ አሰራር የሚያስቀጥል ወይንም ወደሚቀጥለው እርከን የሚያሻግረንን አዲስ ከንቲባ እንመርጣለን። ሁሉም መራጮች በጁን 21 በሚካሄደው ምርጫ መሳተፍ አለባቸው።
ሰሞኑን በቴክሳስ የተከሰተውን ተኩስ በማስመልከት ምን ይላሉ?
እኔም ራሴ አባት ነኝ። አብዛኛው ቤተሰብ እንዳደረገው ባሳለፍነው ሳምንት ከባለቤቴ ጋር ለ6 ዓመት ልጃችንን ስለጉዳዩ በተለይም እንደ ቴክሳሱ ያለ ተኳሽ ካጋጠመ ማድረግ ስላለባት ነገሮች እንዴት ማስረዳት እንደምንችል ስንማከር ነበር። yetኛውም ቤተሰብ እንዲህ ባለ ሃሳብ መጠመድ የለበትም፤ ከምንም በላይ ደሞ ማንኛውም ህፃን እንደዚህ አይነት ሃሳብ ማሰብና መጨነቅ ፈፅሞ የለበትም። በከንቲባነት ተመርጬ ሳገለግል በዋናነት ት/ት ቤቶች ድህንነታቸ የተጠበቀ እንዲሆንና ማንኛውንም ድንገተኛ አደጋ ለመመከት በሚያስችላቸው ቁመና እንዲደራጁ አደርጋለሁ። መንግስትም ለሚፈጠሩ አደጋዎች በፍጥነት መልስ መስጠት የሚያስችለው ቁመና ላይ እንዲገኝ እሰራለሁ። በተጨማሪም እንደ ከንቲባነቴ ከሌሎች የአገራችን ከተሞች ከንቲባዎች ጋር በመሆን የናሽናል ራይፍል አሶሴሽንን ፊትለፊት እጋፈጣለሁ። በአገራችን ተራ ዜጎች፤ የአዕምሮ ህመምተኞችና በአስራዎቹ ያሉ ታዳጊዎች የጦር ሜዳ ጠብመንጃ ይዘው የሚሄዱበት ምንም ምክንያት የለም። ስለሆነም መሳሪያ አምራቾችንና ነጋዴዎችን ማስቆምና ወደከተማችን የሚገቡ ጦር መሳሪዎች ላይም ትብቅ ቀጥጥር እንዲኖር እሰራለሁ።
በዲሲ እየተበራከተ የመጣውን ወንጀል ለመግታት ምን ለመስራት አቅደዋል?
እድገቴ በ80ዎቹና በ90ዎቹ በዲሲ በነበረው ከፍተኛ ቀጥር ያለው ወንጀልና ግድያ በነበረበት ወቅት ነው። አሁንም ታዲያ ወደዚያው እያመራን እንደሆነ ነው የሚታየው። በከተማችን ግደያና ሌሎች ወንጀሎች ላለፉት አምስት አመታት ያለማቋረጥ እያሻቀቡ ይገኛሉ። ይህ በንዲህ እያለ ታዲያ ያሁኗ ከንቲባችን በከተማዋ የተበራከተውን ወንጀል ለመከላከልም ሆነ ለማስቆም እስካሁን ምንም አይነት ዕቅድ የላቸውም። በተቃራኒው እኔ ደግሞ ስራ በጀመርኩብት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ተግባራዊ የማደርገው ሁሉን አቀፍ የሆነ የድህንነት እቅድ አዘጋጅቻለሁ። የፖሊስ ኃይላችን ከድምፅ ረብሻ፤ ትራፊክ ማስከበርና የመሳሰሉ ጉዳዮች በመቀነስ ዋና አላማው የነዋሪወን ደህንነት ማስጠበቅ እንዲሆን እሰራለሁ። በተቸማሪም በርከት ያለ ሁብት ወንጀልን ለመከላከል ያለሙ ፕሮግራሞች ላይ እንዲውሉ እሰራለሁ። ነዋሪዎች ስራ እንዲያገኙ፤ የቤት ችግሮቻቸው እንዲቀረፉ፤ የጤና ፕሮግራሞች እንዲስፋፉና የሱስ ማገገሚያ ፕሮግራሞች እንዲበረክቱ ድጋፍ አደርጋለሁ። በተጨማሪም ለት/ት ቤቶቻችን ድጋፍ በማድረግ፤ ተጨማሪ አቅምን-ያገናዘቡ የመኖሪያ ቤቶችን በማልማት ወንጀልን ከምንጩ ማድረቅ ይቻላል። እናም እንደከንቲባነቴ እነዚህን መሰረታዊ የወንጀል መፈልፈያ ችግሮች ለመቅረፍ በቀርጠኝነት የምሰራ ሲሆን በተጨማሪም ወንጀሎች ሲከሰቱ ፈጥነን ምላሽ የምንሰጥበት እቅድ አዘጋጅቻለሁ። ነዋሪውች በከተማችን ሲኖሩ የደህንነት ስሜት እንዲሰማቸው ብቻ ሳይሆን በትክክል ደህንነታቸው እንዲጠበቅ አደርጋለሁ።
የኑሮ ውድነትን ለመከላከል ምን ሊሰሩ አቅደዋል?
የመጀመሪያ ስራዬ የሚሆነው ለነዋሪዎች የስራ እድሎችን ማመቻቸት ነው። ለዚህ እንዲረዳኝ የጆብስ ጋራንቲ የሚባል ፕሮግራም አዘጋጅቻለሁ። ይህ ፕሮግራም ማንኛውም ስራ መስራት የሚሻ የከተማችን ነዋሪ መስራት እንዲችል ያደርጋል። ከተለማማጅነት በመጀመርም ቢሆን ነዋሪዎች ራሳቸውን በተለያዩ ዘርፎች እንዲያበለጽጉ ያግዛል። በተጨማሪም በከተማችን ላሉ ኑሯቸው ከእጅ ወደ አፍ የሆነባቸውን አነስትኛና መካከልኛ አቅም ያላቸውን የንግድ ተቋማት ድጋፍ እናደርጋለን። የዲሲ አስተዳደር ውስጥ ትልልቅ የንግድ ተቋማት ወደከተማችን እንዲመጡና እንዲሰሩ ድጋፍ የሚያደርግና በከተማው ግብር ከፋይ ነዋሪ የሚደገፍ ተቋም አለን፡፡ እኔ በከንቲባነት ስመረጥ የመጀመሪያ ስራዬ የሚሆነው እዚሁ ዲሲ ውስጥ ያሉ የንግድ ተቋማት ድጋፍ የሚያገኙበትን ተቋም መገንባት ነው። እናም እዚሁ ያሉና ማደግ የሚፈልጉ፤ መስፋፈት የሚፈልጉ፤ ድርጅቶችን እናግዛለን። በከተማችን ያሉ የንግድ ተቋማት ስኬታማ እንዲሆኑ እንሰራለን ምክንያቱም እንዚህ ድርጅቶች ናቸው ሰራተኛ የሚቀጥሩት፤ ወደከተማችን መዋዕለንዋይ የሚያፈሱት። ሌላው በካውንስል አባልነቴ ሳደርገው የቆየሁትና አሁንም የማስቀጥለው የንግድ ተቋማት ተከራይተው የሚሰሩባቸውን ቤቶች እንዲገዟቸውና ከኪራይ እንዲላቀቁ አበክሬ እሰራለሁ። ጥቂት የማይባሉ የንግድ ተቋማት በኪራይ መናር ምክንያት ንግዶቻቸውን እየዘጉ እየለቀቁ ሄደዋል። እኔም ነጋዴዎች የስራ ቦታቸውን እንዲገዙት እገዛ በማድረግ የንግድ ተቋማት ከከተማችን እንዳይወጡ እሰራለሁ።

ለእናቶች የልጆች ማቆያዎችን በማስፋፋት ዙሪያ ምን አቅደዋል?
በአገራቀፍ ደረጃ የህፃናት ትምህርትን በሚመለከት ሰርቻለሁ። በከንቲባነት ስመረጥ ያንን ልምዴን ይዤ ነፃ የህፃናት ትምህርትና ማሳደጊያ በህግ ማዕቀፍ እንዲካተት እሰራለሁ። ወደ ስራ ወይንም ወደ ትምህርት መመልስ የሚፈልጉ ወላጆች በልጆቻቸው ምክንያት እቤት እንዳይወሉ ልጆችም አስፈላጊውን እንክብካቤና ትምህርት በለጋነታቸ እንዲያገኑ የሚያስችላቸውን ፕሮግራም ተግባራዊ አደርጋለሁ። በተጨማሪም የጨቅላ ህፃናት አስተማሪዎችና ተንከባካቢዎች አሁን እንዳለው የመጨረሻውን አነስተኛ ክፍያ ሳይሆን ለስራቸው ተመጣጣኝ ክፍያ እንዲከፈላቸው አደርጋለሁ። እናም ወላጆችም ያለሃሳብ ልጆቻቸውን የህጻናት መዋያ እንዲያቆዩ፤ የህፃናት አስተማሪዎችና ተንከባካቢዎችም ተገቢውን ክፍያ እንዲያገኙና ቤተሰቦቻቸውን ማስተዳደር እንዲቹ እንሰራለን።
በዚህ ምርጫ ለማይሳተፉ ገና የአሜሪካ ዜግነት ላላገኙ ስደተኞች ምን አስበዋል?
በዚህ ምርጫ ለይ መሳተፍ ባትችሉ እንኳ ውጤቱ እናንተንም ላይ ተፀዕኖ ይኖረዋል። ስለሆነም ስለምርጫው ለሌሎች ለሚመርጡ ጓደኞቻችሁ፤ ለቤተሰቦቻችሁ በመንገር፤ በማስረዳት መሳተፍ ትችላላችሁ። በምርጫ የሚሳተፉት እነማን እንደሆኑ እንዲያጣሩና ለስደተኛው ማህበረሰብ፤ ለኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ፤ ለአነስተኛ የንግድ ተቋማት፤ ለት/ት ቤቶቻችን ማን የበለጠ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው፤ ደህንነታችንን ማን የበለጠ እንደሚያስጠብቅልን እንዲመረምሩ ንገሯቸው። እነዚህን ለማሟላት ከኔ የተሻለ ከንቲባ አይኖርም። ለዲሲ አዲስ ቀን ይኖራል፤ ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥረናል፤ ባትመርጡ እንኳ ግባችንን እንድናሳካ ልታግዙን ትችላላችሁ። የምረጡኝ ቅስቀሳዬ በርካታ የድርጅት ድጋፎች አሉት ሆኖም በጣም ወሳኙ ድጋፍ ግለሰቦች ከሚያውቋቸው ሰዎች የሚያገኙት መረጃ ነው። እናም እናንተም ሮበርትን አቀዋለሁ፤ ንግግሩን ሰምቻለሁ ይህ ሰው ምርጫዬ ነው ብላችሁ ለወዳጅ ዘመድ ከነገራቸሁ ትልቅ ውጤት ይኖረዋል።
የመኖሪያ ቤት ተደራሽነትን ለማስፋት ምን ሊሰሩ አቅደዋል?
ብዙ ዘመዶቼና ጓደኞቼ በኑሮ ውድነት ምክንያት ከዲሲ ተገፍተው ወተዋል። በርከት ያሉ ቤተሰቦች ኑሮን ለማሸነፍ ሲቸገሩ፤ ከመኖሪያ ቤታችን ልንፈናቀልና ጎዳና ልንወጣ ነው ብለው ዘውትር በስጋት የሚኖሩ ቤተሰቦችን አይቻለሁ። ይህን በሚመለከት እንደከንቲባነቴ ዋና ተግባሬ የሚሆነው ታዲያ ቤት አልባነተን/ የጎዳና ህይወትን በዘላቂነት ማስወገድ ነው። ይህን ግብ ለማሳካት ታዲያ የቤት ኪራያቸውን መክፈል ላልቻሉ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ mefthie new ነው ምክንያቱ ደግሞ የቤት አልባነትን ሳይከሰት በፊት ሰዎች ጎዳና ሳይወጡ በፊት መከላከል ከወጪ አንፃር ርካሽ ነው። እናም የኪራይ ድጎማ ፕሮግራሞቻችንን እናስፋፋለን፤ ማንኛውም ተከራይ ለኑሮ በማይመች ሁኔታ እንዳይኖር ባለፀጋ ኪራይ ሰብሳቢዎችን ፊትለፊት እንጋፈጣለን፤ ከምንም በላይ ግን ነዋሪው የሰዎችን የለት’ተለት ችግሮች የሚረዳ መሪ መምረጥ ይኖርበታል። የአሁኗ ከንቲባ ከነዋሪዎች የዕለት ተለት ችግር እጅግ የራቁ ናቸው። እኔ ለነዋሪው፤ ለስደተኛው ማህበረሰብ ተጨማሪ ድጋፍ እንዲኖር ስታገል የአሁኗ ከንቲባችን ግን እርዳታ አያስፈልጋቸውም፤ ስራ ፈልገው ይያዙ ብለዋል። ይሄ ትክክለኛ ምላሽ ነው ብዬ አላምንም። ነዋሪው ኑሮን ለማሸነፍ ከአንድ በላይ ስራ እየሰሩ እንኳን ኑሮን ማሸነፍ አልቻሉም። ይሄ በከተማችን በፍፁም መሆን የሌለበት ነገር ነው። ይህ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ መንግሰ ጣልጋ መግባትና ለችግሩ የመፍትሄ አቅጣጫ መስጠት አለበት ብኤ አምናለሁ።
እንግሊዝኛ ቋንቋ ለማይችሉ ነዋሪዎች አሁን ካለው አገልግሎት ሌላ ምን የታሰበ ነገር አለ?
እንደካውንስል አባልነቴ በተለያዩ ቋንቋዎች የትርጉም ስራዎች እንዲሰሩ በመንግስት ተቋማት ያሉ አገልግሎቶች አስተርጓሚዎች እንዲመደቡ የገንዘብ ድጋፍ አድርጌያለሁ። በተጨማሪ ደግሞ የከንቲባው የመህበረሰብ ጉዳዮች ቢሮ ላይ ስር ነቀል ለውጥ እንዲኖር እፈልጋለሁ። እነዚህ ቢሮዎች በዋናነት እታች ማህበረሰቡ ድረስ ወርደው የማህበረሰቡን የልብትርታ ማደመጥ አለባቸው። ከነዚህ ቢሮዎች አንዱ የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ነው እናም ከንቲባ ሆኜ ስመረጥ ይህ ቢሮ ከከተማዋ የአፍሪካ ማህበረሰብ ጋር በቅርብ እንዲሰራ፤ የቋንቋ ተርጉም አገልግሎትና ተደራሽነት እንዲኖርና የነዋሪውን ችግሮች እንዲያዳምጥ አቅጣጫ ይቀመጣል። ይህም ቢሮው እናንተን እንዲዳምጥና አለብን የምትሏቸውን ችግሮች ደግሞ ለእኔ እንዲያደርስ በማድረግ እንደድልድይ እንዲያገለግል ተደርጎ ይዋቀራል።
በመጨረሻ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት አለ?
በመጨረሻም ማለት የምፈልገው ይህ በጣም ወሳኝ ምርጫ ነው። እኔን በከንቲባነት ከመረጣችሁ ሁሌም ችግራችሁን የሚያዳምጥ፤ ለነዋሪዎቹ ጆሮ የሚሰጥ፤ ከምንም በላይ ደግሞ ለችግሮቻችን መፍትሄ ለመስጠት በሙሉ ሃይሉ የሚሰራ ከንቲባ ይኖራችኋል። ከተማችን እጅግ በጣም ትልቅ ኃብት አላት። አመታዊ በጀታችን 20 ቢልዮን ዶላር ነው። ለችግሮቻችን መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችለን አቅም አለን። ሆኖም በስነስርዓት የታነፀና በትኩረት የሚሰራ መንግስት; በቀላሉ የምታገኙት፤ ከህዝብ ያልራቀ የነዋሪውን ችግር የሚረዳ ከንቲባ ያሰፍልገናል። ለዚህ ደግሞ ከእኔ የተሻለ tewedadari አይገኝም። በዚህ ወሳኝ ጊዜም ምን መደረግ እንዳለበት በሚገባ እረዳለሁ። ይህን ከግንዛቤ በማስገባት እንድትመርጡኝ እጠይቃለሁ። በተለያየ ምክንያት የማትመርጡ ከሆነም ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ እንዲመርጡኝ ንገሯቸው። አመሰግናለሁ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት