12/12/2024
Animal Clinic Illustration Instagram posts

ሰሞኑን ፌርፋክስ ካውንቲ ኤከትኒክ ፓርክ (7900 block of Carrleigh Parkway) 4 ሰዎች የነከሰው ካዮቲ የእብድ ውሻ በሽታ ተገኝቶበታል። ይህን ተከትሎ የካውንቲው የጤና ቢሮ ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ (06/04/2022 ና 06/05/2022) ማንኛውም ነዋሪ ወይንም እንስሣ ከማንኛውም አይነት ካዮቲ ጋር ተነካክቶ ከነበረ፤ ተነክሶ ከነበረ፤ ተቧጭሮ ከነበረ፤ የፌርፋክስ ካውንቲ የጤና ቢሮ የእብድ ውሻ ክፍል በ703-246-2433, TTY 711 በአስቸኳይ እንዲደውልና እንዲያስታውቅ ተጠይቋል።

https://www.fairfaxcounty.gov/health/residents-who-encountered-coyote-accotink-parkspringfield-area-asked-contact-health-department

ስለ እብድ ውሻ በሽታ በጥቂቱ ከዊኪፒዲያ

እብድ ውሻ በሽታ የየቫይረስ በሽታ ሆኖ ከፍተኛ የየአንጎል መጉረብረብን በሰዎች እና በሌሎች ደመ-ሞቃት እንስሳት ላይ የሚያስከትል ነው።[1] ቅድሚያ ምልክቶቹ ትኩሳት እና በተነከሱበት ቦታ ማሳከክ/ማቃጠልን ያካትታል።[1] እነዚህ ምልክቶች ከሚከተሉት አንድ ወይም የበለጡ ምልክቶች አስከትለው ይመጣሉ:- ሃይል የታከለባቸው የሰውነት እንቅስቃሴዎች፣ ከቁጥጥር ወጭ የሆ መሸበር፣ የውሀ ፍራቻ, የሰውነት ክፍለን ለማንቀሳቀስ አለመቻል፣ ግራ መጋባት፣ እና ህሊናን መሳት።[1] ምልክቶቹ ከታዩ በኋላ፣ የእብድ ውሻ በሽታ በአብላጫው ሁልጊዜ ሞትን ያስከትላል። [1] በበሽታው በመያዘዎ እና ምልክቶቹ መታየት የሚጀምሩበት የጊዜ ገደብ በአብዛኛውን ጊዜ ከአንድ እሰከ ሶስት ወራት ባሉት ጊዜ ውስጥ ነው። ሆኖም ግን፣ ይህ የጊዜ ገደብ ከሳምንት ባነሰ እና ከአመት በበለጠ ጊዜ ሊለያይ ይችላል። [1] የጊዜ ገደቡ የሚወስነው የበሽታ አምጭው ረቂቅ ህዋስ ወደ የማዕከላዊ የነርብ ስርዓትለመድረስ በሚፈጅበት እርቀት ነው።[2]
የእብድ ውሻ በሽታ ወደ ሰዎች የሚተላለፈው በሌሎች እንስሳት ነው። በበሽታው የተበከለ እንስሳ ሌላ እንስሳ ወይም ሰው ሲቧጭር ወይም ሲናከስ የእብድ ወሻ በሽታ ሊተላለፍ ይችላል። [1] የተበከለ እንስሳ ምራቅ ከሌላ እንስሳ ወይም ሰው የሰውነት ፈሳሽ አመንጭ ህዋስ ያሉበት ማስተላለፊያ ጋር ከተነካካ የእብድ ወሻ በሽታ ሊተላለፍ ይችላል።[1] አብዛኛዎቹ በሰዎች ላይ የተከሰት የእብድ ወሻ በሽታዎች መንስሄዎች የውሻ ንክሻ ናቸው።[1] በአብዛኛው ውሾች የእብድ ውሻ በሽታ ባለባቸው ሀገራት ከ99% በላይ የእብድ ውሻ በሽታ ክስተቶች መንስኤዎች የውሻ ንክሻዎች ናቸው። [3] በአሜሪካዎች ውስጥ፣ የሌሊት ወፎች በአብላጫ የተለመደ የእብድ ውሻ በሽታ መንስኤ ናቸው፣ እናም ሰዎች ላይ ከ5% በታች የእብድ ውሻ በሽታ ክስተቶች መንስኤ ውሾች ናቸው።[1][3] ረጃጅም የፊት ጥርስ ያላቸው ትንንሽ አጥቢ እንስሳት/አይጥ/ሽኮኮ/.. በእበድ ወሻ በሽታ የመያዝ እድላቸው በጣም ኢሚንት ነው። [3] የእብድ ወሻ በሽታ ረቂቅ ህዋስ ወደ አንጎል የሚጓዘው ፐርፈሪያል ነርብስበመከተል ነው። በሽታው ሊታወቅ የሚችለው ምልክቶቹ ከጀመሩ በኋላ ነው። [1]
የተወሰነ ቁጥር ባለቸው የአለም ከፍሎች የእንስሳ ቁጥጥር እና ክትባት መርሀግብሮች በውሻ የሚመጣ የእብድ ውሻ በሽታዎችን ተጋላጭነት ቀንሰዋል። [1] ከፍተኛ ተጋለጭነት ላለባቸው ሰዎች ለበሽታው ከመጋለጣቸው በፊት አስቀድሞ የመከላከያ ክትባትን መስጠት ይመከራል። ከፍተኛ-ተጋላጭ ቡድን ከሌሊት ወፎች ጋር የሚሰሩ ወይም ለረዥም ጊዜያት የእብድ ወሻ በሽታ በአብዛኛው የሚከሰትበት ቦታ የሚሰሩትን ሰዎች ያካትታል። [1] ለእብድ ወሻ በሽታ ለተጠቁ ሰዎች፣ የእብድ ውሻ በሽታ ክትባት እና አንዳንድ ጊዜም የእብድ ወሻ በሽታ ኢሚዩኖግሎቢን ታካሚው የእብድ ውሻ በሽታ ምልክቶች ከመታየታቸው በፊት ህክምናውን ከአገኘ በሽታውን ለመከላከል ወጤታማ ነው። [1] የተነከሰውን እና የተቧጨረውን ቦታ ለ15 ደቂቃ በውሃ እና በሳሙና ማጠብ፣ ፕሮቪዳን አዮዲን, ወይም የንጽህና መጠበቂያ ፈሳሾች ቫይረሱን ሊገሉት ስለሚችሉ እና እንዲሁም የእብድ ወሻ በሽታን መተላለፍን ለመከላለከል በተወሰነ መልኩ ወጤታማ ናቸው።[1] ጥቂት ሰዎች ብቻ የእብድ ወሻ በሽታን ተይዘው ተርፈዋል እናም ይህ የሆነው በመጠነ ሰፊ ህከምና ፣ ሚልዋዪኪ ፕሮቶኮልተብሎ በሚጠራው ነው።[4]
የእብድ ውሻ በሽታ በአለም ዙሪያ በአመት ከ26,000 እሰከ 55,000 ሞቶች ምክንያት ነው።[1][5] ከ95% በላይ እነዚህ ሞቶች የተከሰቱት በኢሲያ እና አፍሪቃነው።[1] የእብድ ውሻ በሽታ ከ150 ሀገራት በላይ እና ከአንታርቲካ በቀር በሁሉም አሀጉራት ይገኛል። [1] ከ3 ቢሊዮን ሰዎች በላይ የእብድ ወሻ በሽታ በሚከሰትበት የአለማችን ከፍሎች ውስጥ ይኖራሉ።[1] እጅግ በአብዛኛው አውሮፓ እና አውስትራሊያ፣ የእብድ ወሻ በሽታ የሚገኘው በሌሊት ወፎች ላይ ነው። [6] በዙ ትናንሽ የደሴት ሀገራት ጭራሹን የእብድ ውሻ በሽታ የለባቸውም።[7]

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት