ሞንጎምሪ ካውንቲ በመጪው ቅዳሜ 06/11/2022 ከጠዋቱ 10 ሰዓት ጅምሮ እስከ ከሰዓት 2 ሰዓት የሚዘልቅ የከባድ መኪና ሾፌሮችን ለመመልመል፤ የከባድ መኪና ሹፍርና (CDL) ፍቃድ ለሌላቸው ደሞ ፍቃድ የሚያገኙበትን መንገድ የሚያመቻችና ለስራ ለማብቃት የሚያስችል ከከባድ መኪና ሹፍርና ጋር የተያያዙ ጠቃሚ መረጃዎች የሚተላለፉበት ፕሮግራም አዘጋጅቷል። ማንኛውም እድሜው 18 አመት የሆነውና ስራ ፈላጊ የካውንቲው ነዋሪ ቢሆንም ባይሆንም በዚህ ፕሮግራም በመሳተፍ ከከባድ መኪና ጋር በተያያዘ ልምድ ካላቸው ባለሞያዎች ጋር መገናኘትና መረጃ ማግኘት ይችላል።
የሞንጎምሪ ካውንቲ በፕሮግራሙ መሳተፍ ለሚሹ እየከፈለ የሚያስተምር ሲሆን ከሹፍርና ውጭ በዌርሃውስ ሰራተኝነት፤ በሜካኒክነት፤ በባስ ሾፌርነትና በመሳሰሉት ተጓዳኝ ዘርፎችም ተመሳሳይ አገልግሎት ይሰጣል። ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ይጫኑ።