06/17/2022
በቀጣይ ዙር የነፃ ኮምፒውተር ምዝገባ መቼ እንደሚጀምር በእርግጠኛ አናውቅም። ግን ከስር በፎቶ እንደሚታየው እስከ ሜይ 31 ባለው መረጃ ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ኮምፒውተሮች ይታዘዛሉ ተብሏል። እስካሁን 3556 ኮምፒውተሮች ለሞንጎምሪ ካውንቲ ነዋሪዎች ታድለዋል፡፡ 6252 ሰው ደሞ ተመዝግቦ ተራ እየጠበቀ ይገኛል።
ካውንቲው በቀጣይ ኮምፒውተሮችን ለማደል መቼ ምዝገባ እንደሚጀምር ባይታወቅም የታዘዙት 29984 ላፕቶፖች ግን ወደነዋሪ መተላለፋቸው አይቀርም። እናም ሁለተኛ ዙር ምዝገባ መኖሩ አይቀርም።
እኛም ተከታትለን እናሳውቃችኋለን።