ማንኛውም እድሜው ከ16 ዓመት በላይ የሆነና የሞንጎምሪ ካውንቲ ነዋሪ ሆኖ የአሜሪካ ዜግነት ያለው ሰው፤ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መፃፍ፤ መናገርና ማንበብ የሚችል (አማርኛ ከቻለ በጣም አሪፍ) እና ከትምህርት ቤቶች/ከህፃናት አካባቢ እንዳይገኝ በህግ ያልተከለከለ ሰው ሊሳተፍበት የሚገባ የዜግነት ግዴታዎች አንዱ በሆነው የምርጫ አስተባባሪነት ለመስራት ከፈለጉ ይህን ሊንክ ተጭነው ይመዝገቡ። ዝርዝር መረጃውን ከፈለጉ ደሞ በዚህ ሊንክ ይሂዱ። የመመዝገቢያ የመጨረሻው ቀን ጁን 28 ነው።
በፖስታ ቤት መምረጥ ከፈለጉ የሜይል-ኢን ባሎት መጠየቂያ የመጨረሻ ቀን ጁላይ 12 ነው። በፖስታ ቤት ለመምረጥ ሜይል-ኢን ባሎት ለመጠየቅ ይህን ይጫኑ።
በተያያዘ ደሞ በቀጣዩ ምርጫ ላይ የሜሪላንድን ጋቨርነር ሊውቴናንት ጋቨርነር፤ ካውንቲ ካውንስል፤ ካውንቲ ኤግዚኪውቲቭ፤ ዩ.ኤስ. ሴናተር፤ ኮንግረስ እና የመሳሰሉትን መሪዎች ለመምረጥ የተመዘገበ ፓርቲ አባል (ወይ ሪፐብሊካን ወይ ዴሞክራት) መሆን ይጠበቅባችኋል። እስካሁን ካልተመዘገባችሁ ወደ 77788 CHECK ብላችሁ ቴክስት በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ።
ከምርጫ ምዝገባ ጋር በተያያዘ ለበለጠ መረጃ ሊንኩን ተከትለው ይሂዱ።