በዚህ በጋ ፓርቲ ሊያዘጋጁ ካሰቡና ታዳሚዎችዎን ማስደመም ከፈለጉ የሞንጎምሪ ፓርኮች የኮክቴል መጠጦች ቅመማና ዝግጅት ስልጠና አዘጋጅቷል። ይህ የኮክቴል መጠጥ ቅመማ ፕሮግራም ጁላይ 13 ከ6፡00-8፡00 pm በሊትል ሴኔካ ክሪክ ሎጅ ይከናወናል። በፕሮግራሙ ላይ በማክሊንተክ ዲስቲሊንግ የተጠመቁ የተለያዩ ኦርጋኒክ መጠጦች ይኖራሉ።
ይህ ስልጠና አራት የኮክቴል አይነቶችን ለማዘጋጀት የሚያበቃ ስልጠና ሲሆን ታዳሚዎች በሰው 48$ እንዲከፍሉ ይጠበቅባቸዋል። 48$ ክፍያው መግቢያንና የማዘጋጃ ግብዓቶችን ያካትታል።
በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ ታዳሚዎች ከ21 ዓመት በላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል። የአልኮል መጠጥ ለማይፈልጉ ሰልጣኞች አልኮል የሌላቸው መጠጦች ተዘጋጅተዋል።
ለመመዝገብ ይህን ሊንክ ይጫኑ።