የሞንጎምሪ ካውንቲ ዘንድሮ የጁላይ 4 የነፃነት በዓልን በማስመልከት 2 የርችት ፍንዳታ ፕሮግራሞች አዘጋጅቷል። ከነዚህም አንዱ ዛሬ 07/02/2022 ሲሆን ሌላኛው ሰኞ 07/04/2022 ይደረጋል ሲሉ የካውንቲው ኤክስኪውቲቭ አቶ ማርክ ኤልሪች አስታውቀዋል።
የርችት ፍንዳታ ፕሮግራሞቹ በሚከተሉት ቦታዎች ከምሽቱ 9፡15 ላይ ይከናወናሉ
ከርችት ፕሮግራም በተጨማሪ በፕሮግራሞቹ ላይ የተለያዩ የሙዚቃ ድግሶች (ኮንሰርቶች) ይኖራሉ። የዛሬው ፕሮግራም በጆ ፋሌሮ የላቲን የጃዝ ባንድ ሙዚቃዎች ከምሽቱ 6 ሰዓት የሚጀምር ሲሆን 7፡30 ጀምሮ ደሞ ኳይት ፋየር የተባል የሶውልና አር ኤንድ ቢ እንዲሁም የሮክ ባንድ ታዳሚዎችን ያዝናናል።
በፕሮግራሙ አካባቢ ፓርኪንግ ባለመኖሩ ከዊተን ሞል ወደ ፕሮግራሙ የሚያጓጉዙ የነፃ የባስና የሸትል አገልግሎቶች ተዘጋጅተዋል
የሰኞው ፕሮግራም ከምሽቱ 7 ሰዓት የሚጀምር ሲሆን በቦታው ነፃ ፓርኪንግ ተዘጋጅቷል።