07/19/2022 – ዋሽንግተን ዲሲ — የዲሲ ከንቲባ ሚውሪዬል ባውዘር በቀጣይ ሊተገብሩት ላሰቡት የፍትኃዊነት ፕሮግራም ነዋሪዎችን ለማሳተፍ ፕሮግራም ይዘዋል። በዚህ ፕሮግራም ላይ በዋሽንግተን ዲሲ ለሚኖሩና አናሳ ለሆኑ ማህበረሰቦች የኃብት ፍትኃዊነትን ለማረጋገጥ በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ተግባራዊ የሚደረጉ ፕሮጀክቶችን ይወሰናሉ።
በዚህ ፕሮግራም ላይ እስካሁን በተለያዩ ምክንያቶች የተገለሉ ማህበረሰቦችን አቃፊ የሆኑና ሁሉም የከተማው ነዋሪን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮግራሞችን ለማውጣት የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ነው።
እነዚህ ምክክሮች በዋናነት 4 ግቦች ይኖራቸዋል
1. የዲሲ መንግስት ሰራተኞች ጥልቅ የሆነ ይፍትኃዊነት እውቀት ይኖራቸዋል
2. በዘር፤ በቋንቋና በቆዳ ቀለም የሚደርሱ መገለሎችን ማስወገድ
3. የተለያዩ ማህበረሰቦችን ህብረቶችን/ተቋማትን መፍጠርና ያሉትን ማጠናከር
4. የዲሲ መንግስት ፍትኃዊ ቀጣሪ እንዲሆንና ሰራተኞቹም በፍትኃዊነት ለእድገት፤ የደሞዝ ማሻሻያ እንዲያገኙና በስራቸው እንዲቆዩ ማስቻል ናቸው።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያውያንን ጉዳይ የሚመለከተው የከንቲባዋየአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ ኦገስት 3 ከ6 – 8pm ከከተማዋ አፍሪካዊ ነዋሪዎችጋ ለመማከር ቀጠሮ ይዟል።በዚህ ውይይት ላይ ማንኛውም ሰው መሳተፍ ይችላል። ከሜሪላንድና ቨርጂንያም መሳተፍ ይቻላል። የስብሰባ ቦታው Frank D. Reeves Center, 2000 14th St., NW, Edna Frazier Community Room. ነው። ለመሳተፍ ምዝገባ ያስፈልጋል።ለመመዝገብ ይህን ይጭኑ።
ሙሉ መልዕክቱን ይህን በመጫን ያገኙታል።