ብሬድ ፎር ዘ ሲቲ ለዘንድሮ አመትበዓል ስጦታዎችን ለዲሲ ነዋሪዎች አዘጋጅቷል።
እነዚህ ስጦታዎች የ50$ ዴቢት ካርድ፣ ተርኪና የተለመዱ የአትክልትና ፍራፍሬዎች ከስፔሻል የበአል ጥቅሎችጋ አዘጋጅቷል። ይህ ፕሮግራም ለዲሲ ነዋሪዎች ብቻ ነው። ስጦታዎቹ ከኖቨምበር 1-23፣ 2022 (ሰኞ ኖቨምበር 11ን ሳያካትት) ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 9ሰዓት እስከ ከሰዓት 4 ሰዓት በኖርዝዌስትና ሳውዝኢስት ቢሮዎቹ በመገኘት መውሰድ ይቻላል። ሲመጡ የዲሲ መታወቂያ ይዘው ይምጡ ብለዋል። በተጨማሪም በአንድ ቤተሰብ/ቤት አንድ ስጦታ ብቻ ነው የሚፈቀደው።
አድራሻ
Northwest Center
1525 7th St NWWashington, DC 20001
Southeast Center
1700 Good Hope Rd SEWashington, DC 20020