የአርሊንግተን ካውንቲ ፖሊስ ባሳለፍነው አርብ ኦገስት 11 2023 ከምሽቱ 9፡44 በ1900 ብሎክ ኦፍ ክላሬንደን ቡሌቫርድ አካባቢ በተከሰተ ግጭት አማካኝነት የጠፋ የሰው ነፍስ ላይ ምርመራ እያደረገ እንደሆነ አስታውቋል።
የፖሊስ ምርመረ እንደሚያሳያየው በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ሞፔድ (አነስተኛ ሞተርሳይክል) ከተገቢው ፍጥነት በላይ እያሽከረከረ የነበረው የ44 አመት እድሜ ያለው ሰለሞን ዘለቀ የተባለ የአርሊንግተን ነዋሪ መንገድ ስቶ በመውጣት ከስልክ እንጨትጋ እንደተጋጨና አደጋውን ተከትሎም ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም እዛው ሆስፒታል ለህልፈት እንደተዳረገ ተነግሯል።
የአደጋው ትክክለኛ መንስኤን የማጣራት ስራ ፖሊስ እየሰራ እንደሆነና ተጨማሪ መረጃ ያለው ሰው ለመርማሪዎች በ Slafley@arlingtonva.us ወይንም በ 703-228-4052.ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አድርጓል።
ለመረጃው ብሩክን እናመሰግናለን