የአፎርደብል ሃውሲንግ ቤቶች ለማግኘት የሚሹ ሰዎች ከሴፕቴምበር 11 ጀምሮ እስከ ሴፕቴምበር 17 ኦንላየን ሬንት ካፌ ላይ በመግባት በተጠባባቂነት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ በዚህ ዙር የተጠባባቂ ነዋሪዎችን የሚመዘግቡት አፓርታማዎች የሚከተሉት ናቸው
- ዚ አርደን _ በ 2317 Huntington Avenue, Alexandria, VA 22303 ይገኛል
- ኦቬሽን አት አሮውብሩክ _ በ 1335 Fairfield Ridge Avenue, Herndon VA 20171 ይገኛል
- ማዲሰን ሪጅ _ በ 14806 Rydell Road, Centreville, VA 20121 ይገኛል
- ዚ ሬዚደንስ አት ኖርዝ ሂል _ በ 7250 Nightengale Hill Lane, Alexandria, VA 22306 ይገኛል
ማመልከት የሚፈልጉ ሬንትካፌ ላይ ከሰኞ ሴፕቴምበር 11 ጧት 8 ሰዓት ጀምሮ ማመልከት ይችላሉ፡፡ ለማመልከት ድጋፍ ወይንም እገዛ የሚፈልጉ ደሞ ካውንቲው ጋ በ 703 246 5100 በመደወል ወይንም ወደፌርፋክስ ካውንቲ ቤቶች ልማት ቢሮ 3700 Pender Drive in Fairfax, VA. በአካል በመሄድ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ዜናውን ያገኘነው ከካውንቲው ሪዴቨሎፕመንትና ኃውሲንግ ኦቶሪቲ ነው፡፡ ማመልከቻዎች የሚያስገቡት በሬንት ካፌ ድረ ገጽ ላይ ነው፡፡ ሬንትካፌ ላይ ለመመዝገብና ለማመልከት መርጃ ዶክመንት ይህን ሊንክ ተጭነው ማውረድ ይችላሉ፡፡
ማመልከቻው ሰኞ ሴፕቴምበር 11 2023 ተከፍቷል፡፡ ለማመልከት ሊንኩን ይጫኑ፡፡
ስለዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ በርካታ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘትና የኢትዮጲክ ዲጂታል ጋዜጣ በኢሜይልዎ እንዲደርስዎት ይህን ሊንክ ተጭነው ይመዝገቡ