12/12/2024
Add a heading(1)

የዚህ በአስርት አመታት አንዴ የሚከፈት ምዝገባ ለውስን ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

የአርሊንግተን ካውንቲ ቤቶች ልማት የ2023 ሀውሲንግ ቾይስ ቫውቸር ተጠባባቂዎች ምዝገባ በመጪው ሳምንት ሴፕቴምበር 13 ጅምሮ ያከናውናል። ይህ የፌደራል መንግስት የቤት ኪራይ ድጋፍ ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ ቤተሰቦች የቤት ኪራያቸውን እንደገቢያቸው መጠን እስከ 100% ድረስ ይከፍላል።

የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚዎች በካውንቲው ውስጥ ባሉ የኪራይ ቤቶች በፈለጉት ቤት መኖር ይፈቅድላቸዋል። ይህ ምዝገባ በየ10ና 20 ዓመቱ ብቻ የሚወጣ ሲሆን ከዘንድሮው ምዝገባ በኋላ ቀጣዩ ምዝገባ ከ10 ወይንም ከ20 ዓመት በኋላ ይሆናል ማለት ነው። ካውንቲው በዘንድሮው ምዝገባ 5000 ተጠባባቂዎችን ለመያዝ አቅዷል።

የማመልከቻ ቀን ረቡዕ ሴፕቴምበር 13 2023 ከጧቱ 8 ሰዓት የሚጀምር ሲሆን እስከ ቅዳሜ ሴፕቴምበር 23 ምሽት 11፡59 ይዘልቃል።

በዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን አመልካቾች የአሜሪካ ዜጋ ወይንም ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባለቤት መሆንና የቤተሰባቸው ገቢ ከታች በሰንጠርዡ ከተመለከተው ማለፍ የለበትም ተብሏል።

ለመመዝገብና ለማመልከት ይህን ይጫኑና ፎርሙን ይሙሉ

ለበለጠ መረጃ የካውንቲው ድረ ገጽ ላይ ይህን ሊንክ ተከትለው በመሄድ ያግኙ፡፡

በፌስቡክና ትዊተር ይከተሉን

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት