የፌርፋክስ ፖሊስ በኦክቶበር 25 2023 እኩለ ቀን አካባቢ ከፌርፋክስ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሰራተኞች በደረሰው ጥቆማ በእለቱ ጠዋት ላይ ማንነቱ ያልታወቀ ወንድ በትምህርት ቤቱ ተማሪ የሆነችን ታዳጊ የአውቶቡስ መጠበቂያ ቦታ ላይ ጥቃት እንዳደረሰባት፤ ያለፈቃዷ ትከሻዋን በመንካት፤ የኤልክትሮኒክ ሲጋራ (ቬፕ) በመጋበዝ እንዲሁም ጉንጯን በመሳም እንደሄደ በጥቆማው ተጠቅሷል።
የፌርፋክስ ካውንቲ ፖሊስ መርማሪዎች ኋላ ላይ ባደረጉት ምርመራ ታዲያ ይህን ተግባር ፈጽሟል ያሉትን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉትና ተጠርጣሪው በ3851 Billberry Drive Fairfax, VA 22033 ነዋሪ የሆነው የ31 አመቱ ጊግሳ በቀለ በንጌሳ እንደሆነ በኦክቶበር 27 ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል።
የኢትዮጲክ ባልደረቦች የፌርፋክስ ፖሊስን ተጨማሪ መረጃ ጠይቀው መልስ እየጠበቁ ነው። እንደደረሰ ይቀርባል።
ለመረጃው ኤቫ ብሩክን እናመሰግናለን።
የፌርፋክስ ካውንቲ ፖሊስ መርማሪዎች ኋላ ላይ ባደረጉት ምርመራ ታዲያ ይህን ተግባር ፈጽሟል ያሉትን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር እንዳዋሉትና ተጠርጣሪው በ3851 Billberry Drive Fairfax, VA 22033 ነዋሪ የሆነው የ31 አመቱ ጊግሳ በቀለ በንጌሳ እንደሆነ በኦክቶበር 27 ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል።