የዋሺንግተን ዲሲ ድንገተኛ የቤት ኪራይ ድጋፍ ማመልከቻ ዛሬ ጃንዋሪ 2 2024 እኩለ ቀን ጀምሮ ይከፈታል። በአዲሱ የበጀት አመት ማመልከቻው በየ3 ወሩ የመጀመሪያዎቹን 3500 ማመልከቻዎች ብቻ እንደሚያስተናግድና ልክ 3500 ማመልከቻ እንደተቀበለ የማመልከቻው ድረ-ገጽ እንደሚዘጋ ይታወቃል። በተለይ ከአከራዮቻችሁ የኢቪክሽን ወረቀት ከተቀበላችሁ ይህንን ማመልከቻ ሞልተው በመላክዎት ብቻ የኢቪክሽን ፕሮሰሱ እንዲቆም ያደርግላችኋል።
ይህን ድጋፍ የሚሹ የዲሲ ነዋሪዎች ማመልከቻቸው ቶሎ እንዲያስገቡ ይመከራል። ይህ ዙር ላለፋቸው አመልካቾች ቀጣዩ ዙር የሚከፈተው በኤፕሪል ወር ይሆናል።
ሁሌም ትኩስ መረጃዎቻችንን ለማግኘት በፌስቡክ ይከተሉን