05/04/2024

ተጠባቂው የ2024 የሞንጎምሪ ካውንቲ ትምህርት ቦርድ ምርጫ
በ2023 በርካታ ኢትዮጵያውያንን ከወትሮው ባልተለመደ መልኩ በአሜሪካ በሚኖሩበት አካባቢ ባሉ ፖሊሲዎች ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለማሰማትና መብታቸውን ለማስከበር እንዲሁም ድምጻቸውን ለማሰማት የተሳተፉበትና አገር አቀፍ የሚድያ ሽፋን ያገኘው የሞንጎምሪ ካውንቲ ስርዓተ ትምህርት ፖሊሲን በበላይነት የሚያስተዳድረው የትምህርት ቦርድ ለ2024 ሶስት መቀመጫዎቹ ለምርጫ ይቀርባሉ።

ለነዚህ መቀመጫዎች ከሚወዳደሩት እጩዎች ዘጠኙ ትላንት በካውንቲ ካውንስል አዳራሽ ክርክር አድርገው ነበር፡፡ ከ80% በላይ የሚሆነው የኢትዮጲክ አንባቢ ያሳስበኛል ያለውና የዘንድሮውን ምርጫ ስመርጥ ዋና መመዘኛዬ ነው ያለው ጉዳይ ወላጆች ከሀይማኖታቸውጋ የሚጋጩ ትምህርቶች ላይ ልጆቻቸው እንዳይሳተፉ የማድረግ መብትን ማስወሰን የሚለው ጥያቄ ላይ እጩዎቹ በፎቶው እንደሚታየው መልሰዋል፡፡

ትላንት በክርክሩ ከተሳተፉት ሌሎች እጩ ተወዳዳሪውችን ይህንንና ሌሎች ጥያቄዎች መልስ እንዳገኘን እናቀርባለን፡፡ ስለካውንቲው የትምህርት ቦርድ ምርጫ ዝርዝሩን ይህን ሊንክ ተከትለው በምሄድ ያግኙ https://ethiopique.com/?p=3074
@followers

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *