12/12/2024
የቦይንግ-737-ማክስ-አውሮፕላኖች-የላላ-ብሎን-አላቸው-ተባለ-8

Update: – ይህ ማስጠንቀቂያ ከአርብ 05/10 ጅምሮ ተነስቷል::

———-

የዋሽንግተን ዲሲ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዛሬ ረቡዕ ሜይ 8 2024 ባወጣው ማስጠንቀቂያ በሰሜን ምዕራብ አካባቢ ባለ የውኃ ማከፋፈያ በመሰበሩ ምክንያት በተወሰኑ የከተማው አካባቢዎች ያሉ ደንበኞች ውኃቸውን አፍልተው እንዲጠቀሙ አስጠንቅቋል።


ማስታወቂያ:- በየጊዜው የምናወጣቸውን መረጃዎች ለማግኘት በፌስቡክና … በቴሌግራም ይከታተሉ:: ለወዳጅ ጏደኞችም ይንገሯቸው::


ይህ ማስጠንቀቂያ በእርግጠኛነት ውኃው መበከሉ ስለተረጋገጠ ሳይሆን ለጥንቃቄ እንደሆነም አክለው ገልጸዋል። በዚህም የተነሳ ይህ የውኃ ኃይል ማነስ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች የቧንቧ ውኃቸውን ሳያፈሉ እንዳይጠቀሙ አሳስቧል። የዲሲ ውኃና ፍሳሽ ከነገ ጀምሮ በተከታታይ የውኃ ምርመራ አድርጎ የውኃውን ጤናማነት እስኪያረጋግጥ 2 ቀን ይፈጃል ስለሆነም ይህ ማስጠንቀቂያ እስከ አርብ ሜይ 10 ድረስ ይዘልቃል።

በዚህ እክል የተጠቁት አካባቢዎች ከስር ባለው የአርክ ጂ አይ ኤስ ማፕ ላይ ማየት ይችላሉ።

  • ውኃ አፍልተው እንዲጠቀሙ የተመከሩ የዲሲ አካባቢዎች

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተገቢውን የላቦራቶሪ ምርመራ አድርጎ የውኃውን ጤነኛነት እስኪያረጋግጥ ድረስም ነዋሪዎች የቧንቧ ውኃ ሳያፈሉ እንዳይጠቀሙ መክሯል።

በነዚህ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል?

  • በቧንቧ ውኃ የተሰሩ በረዶዎችንና ሌሎች መጠጦችን ያስወግዱ
  • ውኃ ከቧንቧ ሲወርድ ቀለሙን ከቀየረ ንጹህ ውኃ መፍሰስ እስኪጀምር ቧንቧውን ከፍተው ይተዉት
  • የታወቁ የሊድ ምንጮች ካሉ ቀዝቃዛ ውኃ ለሁለት ደቂቃ ያፍሡ
  • ውኃውን ቢያንስ ለ1 ደቂቃ በደንብ ያፍሉትና አቀዝቅዘው ይጠቀሙ
  • የቀዘቀዘውን ውኃ በንጹህና በተሸፈነ ማስቀመጫ ያኑሩት

በዚህ ወቅት ፈልቶ የቀዘቀዘ ውሃ ወይም የታሸገ ውሃ ብቻ ለሚከተሉት አገልግሎቶች ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡

  • ለመጠጥ
  • ጥርስ ለመቦረሽ
  • ምግብ ለማብሰል እና ማዘጋጀት
  • ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ለማጠብ
  • የሕፃናት ፎርሙላ ለማዘጋጀት
  • በረዶ ለመሥራት
  • ለቤት እንስሳት የመጠጥ ውሃ ለመስጠት
  • በፍጹም የውኃ ማጣሪያ ማሽኖችን ብቻ ተማምነው ውኃ ከማፍላት እንዳይዘናጉ።

ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶች ካሏችሁ ራሳቸውን ከበሽታ እንዲጠብቁ ይህን መረጃ አጋሯቸው።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት