
ዛሬ ማክሰኞ ሜይ 14 2024 የሜሪላንድ ፕራይመሪ ምርጫ የሚደረግበት የመጨረሻ ቀን ነው። በዚህ ምርጫ ለሴኔት እየተወዳደሩ የሚገኙት የፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲዋ አንጀላ ኦልሶብሩክና የዴቪድ ትሮን ፉክክር ተጠባቂ ነው።በተጨማሪም የሞንጎምሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድን ለማስተዳደር እጩ ሆነው በኖቨምበር ለሚደረገው ውድድር የሚቀርቡ እጩዎች ውድድርም እንዲሁ ተጠባቂ ነው። እናንተም በአቅራቢያችሁ ያገለግለኛል የምትሉትን እንድትመርጡ ለማስታወስ እንወዳለን። መልካም ፕራይመሪ።