untitled (instagram post)-1

🎉በመላው ዩናይትድ ስቴትስ ከ900 በላይ የዜና አገልግሎት ሰጪዎች በተሳተፉበትና የገለልተኛ አነስተኛና አካባቢያዊ የዜና ተቋማትን ለመደገፍ ታስቦ በተዘጋጀው የፕሬስ ፎርዋርድ ውድድር ላይ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ከተመረጡ 205 አሸናፊ የዜና ተቋማት መኃከል አንዷ ኢትዮጲክ ሆናለች። ይህ የሽልማት ፕሮግራም በተለይም ከዚህ ቀደም በዜናና ሌሎች መረጃዎት ትኩረት ላላገኙ ማህበረሰቦች አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ተቋማትን ለማገዝ አቅዶ የተዘጋጀ አገር አቀፍ የድጋፍ ፕሮግራም ነው።

ይህ ሽልማት ያለናንተ ተሳትፎ እውን አይሆንም ነበር:: እኛ በተቻለን መጠን በእውቀት ላይ የተመሰረቱና እውነተኛ መረጃዎችን ይዘን ለመምጣት እንጥራለን:: ሆኖም የኛ እውቀት ውስን በመሆኑ አልፎ አልፎ ጥያቄዎች ይዘን ወደ አንባቢዎቻችን እንሄዳለን:: ይህም ኢትዮጲክን ከዜና ተቋም በተጨማሪ የማህበር ዕውቀት ማንሸራሸሪያ መድረክ (town square) እንድትሆን አድርጏታል:: ለዚህም እናንተ በየቀኑ የምትልኩልን መረጃዎች፤ ለጠየቅናችሁ ጥያቄዎች የምትሰጡን በልምድና በእውቀት የተገኘ መልሳችሁ፤ እና የመረዳዳትና መተጋገዝ ርብርቦሽ ማስረጃ ነው:: 

እኛ የኢትዮጲክ ባልደረቦች ይህን ዕውቅና በማግኘታችንና በመላው አሜሪካ ካሉ 205 ምርጥ የዜና ተቋማት ተርታ በመመደባችን ደስ ብሎናል… እናንተንም እናመሰግናለን። እስካሁን ስለ እኛ ያልሰሙ ወዳጅ ዘመዶች ካሏችሁ ንገሯቸው … ይምጡና ይቀላቀሉን። ልታካፍሉን የምትፈልጉት መረጃዎች ወይም ሌሎች ቢያውቁት ይጠቀማሉ የምትሉትም ዕውቀት ካለ ተሳተፉ…. በራችን ክፍት ነው። ስለ ሁሉም ነገር እናመሰግናለን። 

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.