12/12/2024
Untitled

49ኛው የመሪን ኮር ማራቶን ነገ ዕሁድ ኦክቶበር 27 2024 ከጧት 7፡55am ጀምሮ ይከናወናል። በዚህ ታላቅ የሩጫ ውድድር ላይ ከ30 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ፕሮግራም ከዋናው የማራቶን ውድድር በተጨማሪ በውስጡ በርካታ የተለያዩ ውድድሮችንና የመዝናኛ ፕሮግራሞችንም አካቷል።

በዚህ ውድድር ምክንያትም በርካታ መንገዶች በአርሊንግተንና በዲሲ ይዘጋሉ ተብሏል። የሚዘጉ መንገዶችን ለማየት ይህን ሊንክ ይጫኑ። በተጨማሪም ውድድሩን ለመመልከት የመመልከቻ ቦታዎች የተዘጋጀ ሲሆን ይህን ሊንክ በመጫን ያገኙታል። ውድድሩ በሚከናወንበት መንገድ ላይ መኪና ማቆም ክልክል ነው። የትራንስፖርት ችግርን ለማስቀርተና ተሳታፊዎች ያለችግር በውድድር ቦታው እንዲገኙ ለማገዝም ሜትሮ ከቀድሞው በተለየበጊዜ 5am ላይ ስራ ይጀምራል።

Image Credit: Marine Corps Marathon Organization

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት