01/07/2025
Screenshot 2025-01-05 at 10.12.28 PM

ነገ ሰኞ ይኖራል ተብሎ የሚጠበቀውን የበረዶ ስቶርም በማስመልከት የሞንጎምሪ ካውንቲ ይህን መግለጫ አውጥቷል። ከእኩለለሊት በኋላ መንገድ ዳር መኪና እንዳታቆሙ ተብሏል። የግድ ማቆም ካለባችሁም ሰኞ ጃንዋሪ 6 ጎዶሎ ቁጥር መደዳ አድራሻዎች ባሉበት የመንገዱ መደዳ ብቻ አቁሙ ማክሰኞ ጃንዋሪ 7 ደሞ በሙሉ ቁጥር በኩል ብቻ አቁሙ ሲል አክሎ የካውንቲው የህዝብ መኪና ማቆሚያዎች በነጻ ማቆም እንደሚቻል ና እንደሚበረታታ አክሏል።


በካውንቲው ባሉ የበረዶ የድንገተኛ መንገዶች (snow emergency routes) በፍጹም ማቆም እንደማይቻልና ቆመው የተገኙ መኪኖች ቶው ሊደረጉ እንደሚችሉ ከመሸ ባወጡት መግለጫ አሳውቀዋል። ሙሉ መግለጫው ከስር ተያይዟል።

የሞንጎምሪ ካውንቲ የድንገተኛ በረዶ አዋጅ

በተጨማሪም ነዋሪዎች በረዶ በጣለ በ24 ሰዓት ውስጥበረዶውን ከደጃፋቸው ማጽዳት እንዳለባቸው ተገልጿል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *