የዲሲ ዲፓርትመንት ፎር-ኃየር ቪኺክልስ (Department of For-Hire Vehicles (DFHV)) የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር ዛሬ ያወጡትን የድንገተኛ በረዶ አዋጅ ተከትሎ ታክሲዎችና ሌሎች በዲሲ የኮንትራት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በሙሉ የዋጋ ጭማሪ እንዲያደርጉ ፈቅዶላቸዋል። በዚህም መሰረት ማንኛውም የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ሰኞ ጃንዋሪ 6 ከእኩለ ለሊት (12፡00am) ጀምሮ ከመደበኛ የትራንስፖርት ዋጋቸው በተጨማሪ ወጥ የሆነ የ15$ ጭማሪ እንዲያደርጉ ይፈቅዳል። ይህ ጭማሪ መነሻቸው ከዲሲ ለሆኑ አገልግሎቶች ብቻ ተግባራዊ ይሆናል። መረጃውን ያደረሰንን ብርሀኑን እናመሰግናለን።