01/07/2025
የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር የድንገተኛ በረዶ አደጋ አዋጅ አወጁ

የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር የድንገተኛ በረዶ አደጋ አዋጅ አወጁ

ከንቲባዋ ከእሁድ ማምሻ ጀምሮ እስከ ሰኞ ይኖራል ተብሎ በሚጠበቀው የበረዶ ውሽንፍር ምክንያት ሊኖር የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞቻቸውን በተጠንቀቅ እንዲዘጋጁ ያዘዙ ሲሆን ይህ አዋጅ እስከ ማክሰኞ ምሽት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የበረዶ የድንገተኛ መንገዶች (snow emergency routes) ምስል ከዲሲ መንግስት ድረ-ገጽ

በዚህ የአዋጅ ወቅትም አሽከርካሪዎች ለበረዶ የድንገተኛ መንገዶች (snow emergency routes) ላይ መኪኖቻቸውን እንዳያቆሙ አዘዋል። ቆመው የተገኙ መኪኖች ቶው እንደሚደረጉም ተናግረዋል።


በዋሽንግተን ዲሲ የበረዶ የድንገተኛ መንገዶች (snow emergency routes) የሚባሉት የትኞቹ እንደሆኑ ለማወቅ ከስር ያለውን ዶክመንት ዳውንሎድ በማድረግ ማየት ይችላሉ። አሽከርካሪዎች ከአሁን ጀምሮ በፍጥነት መኪናዎቻቸውን ከነዚህ መንገዶች እንዲያነሱ ከንቲባዋ አሳውቀዋል። ከዛሬ ዕሁድ 9pm ጀምሮ በበረዶ የድንገተኛ መንገዶች (snow emergency routes) ላይ ቆመው የተገኙ መኪኖች ቶው የሚደረጉ ሲሆን የት እንዳሉ ለማወቅ አሽከርካሪዎች በስልክ ቁጥር (202) 541-6083 በመደወል ወይም በዚህ ሊንክ በመሄድ ያለበትን ቦታ ማወቅ ይቻላል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *