
እባካችሁ ሼር አርጉት ይህንን – – – መጪው የትራምፕ አስተዳደር በመጀመሪያዎቹ ቀናት ያለፍቃድ ስራ የሚሰሩ ስደተኞችንና ያለ ህጋዊ ወረቀት በዲሲና አካባቢው ያሉ ስደተኞች የማፈስ እርምጃ ለማድረግ እንዳቀደና ለዚህም እንዲረዳው የሰው ሃይልና ሌሎች ድጋፎችን ከ ICE እንደጠየቀ የ NBC Washington ዘገባ ያሳያል። የሚመለከታችሁ ካላችሁ ጥንቃቄ አድርጉ ብለን ከለጠፍን በኋላ በርካቶች ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባችሁ እንድንመክራችሁ ጠይቃችሁናል። ለሁላችሁም አንድ በአንድ ከምንመልስ ከሳምንታት በፊት ካዘጋጀነው ዌቢናር ላይ ይህን ቁራጭ ቪዲዮ እንድትመለከቱ ጋብዘናችኋል። ለሚመለከታቸው አጋሩ።
ሙሉ ዌቢናሩን ለማየት ደግሞ ይህን ሊንክ ተከትለው ይሂዱ …