
በቨርጂንያ ፌርፋክስ ካውንቲ የአፎርደብል ሃውሲንግ ቤቶች ለማግኘት የሚሹ ሰዎች ከዛሬ ሰኞ ጃንዋሪ 13 2025 ጀምሮ እስከ ዕሁድ ጃንዋሪ 19 2025 ኦንላየን ሬንት-ካፌ ላይ በመግባት በተጠባባቂነት መመዝገብ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ በዚህ የተጠባባቂ ምዝገባ ላይ በመመዝገብ በቀጣይ በነዚህ አፓርታማዎች በሚኖሩ ክፍት ቦታዎች ላይ ተመዝጋቢዎች በሎተሪ መልክ እድለኞች የቤት ባለቤት ይሆናሉ።


በዚህ ዙር የተጠባባቂ ነዋሪዎችን የሚመዘግቡት ዘጠኝ አፓርታማዎች ሲሆኑ ሰባቱ ለማንኛውም ዕድሜው ከ18 ኣመት በላይ ለሆነ ሰው እና የተቀሩት ሁለቱ ደሞ ዕድሜያቸው ከ62 ዓመት በላይ ለሆኑ አዛውንቶች ብቻ ነው፡፡ እነዚህ አፓርታማዎች ባለ ስቱዲዮ፤ ባለ አንድ መኝታ፤ ባለ ሁለት መኝታና ባለ ሶስት መኝታ ሲሆኑ ዝርዝራቸው እንደሚከተለው ነው፡፡
- Autumn Willow, one and two-bedroom apartments 13175 Autumn Willow Drive, Fairfax, VA 22030 571-609-3090
- Herndon Harbor House, one-bedroom apartments Grace Street and Jorss Place, Herndon, VA 20170 703-904-9444
- Lindsay Hill, one and two-bedroom apartments 8915 Pink Carnation Court, Lorton, VA 22079 703-646-4701
- North Hill Senior Residences, two-bedroom apartments 7245 Nightingale Lane, Alexandria, VA 22306 571-410-0235
- Oakwood Meadow, one and two-bedroom apartments 5815 South Van Dorn Street, Alexandria, VA 22310 571-946-9694
- Coppermine, two-bedroom apartments 13395 Coppermine Road, Herndon, VA 20171 703-793-0336
- Lake Anne House, efficiency, one and two-bedroom apartments 11444 North Shore Drive, Reston, VA 20190 571-901-1319
- One University, two-bedroom apartments 4518 University Drive, Fairfax, VA 22030 703-942-6610
- Lincolnia Senior Apartments, efficiency/studios 4710 N. Chambliss Street, Alexandria, VA 22312703-914-0330

በነዚህ አፓርታማዎች ተጠቃሚ ለመሆን ነዋሪዎች ገቢያቸው ከተፈቀደው በላይ መሆን የለበትም። በፌርፋክስ ካውንቲ በዚህ እድል ለመጠቀም ለማነጻጸሪያነት የሚቀርበው የገቢ ደረጃ እንደሚከተለው ተቀምጧል።

ይህን ማመልከቻ በሬንት ካፌ ለማመልከት የሚረዳ በካውንቲው የተዘጋጀ የማመልከቻ አጋዥ ዶክመንት ለማየት ከስር ያለውን ፋይል ማየት ይቻላል።
በዚህ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆንና በተጠባባቂነት ለመመዝገብ ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
ተጨማሪ መረጃ ይህን ተጭነው ከካውንቲው ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
