@ethiopique202

በሜሪላንድ የተወካዮች ምክር ቤት የፕሪንስ ጆርጅ ካንውቲን የሚገኘውን 22ኛ ዲስትሪክት ወክለው የተመረጡት ተወካይ ኒኮል ዊልያምስ ፌብሯሪ 4 2025 አንድ ረቂቅ የህግ ማሻሻያ አቅርበዋል፡፡ ይህ ሀውስ ቢል 380 የተባለ ረቂቅ ህግም አሁን በሜሪላንድ ህግ በወንጀል የሚያስጠይቀውን በትምህርት ቤቶች ውስጥ በቬንዲንግ ማሽን የኮንዶምና የመሳሰሉ የወሊድ መቆጣጠሪያ መሸጥን እንዲወገድ የሚጠይቅ ህግ ነው፡፡  

አሁን ባለው ህግ በሜሪላንድ በተለይም በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ሴክሽን 10-105 መሰረት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ኮንዶምና የመሳሰሉ ይወሊድ መቆጣጠሪዎችን በቬንዲንግ ማሽን መሸጥ በደንብ መተላለፍ የሚያስቀጣ ሲሆን ድርጊቱን እንደፈጸመ የተረጋገጠበት ድርጅት ወይንም ሰውም እስከ 1000 ዶላር ድረስ ሊቀጣ እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ታዲይ ይህ ህግ እንዲሰረዝና ይጠይቃል፡፡ ይህን ህግ እንዲሰረዝ የሚደግፉ ሰዎች ይህ ህግ ኋላ ቀርና ጊዜውን ያላገናዘበ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ህጉ በመሻሩም የወሊድ መቆጣጠሪያ አማራጮችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚቻል ይናገራሉ፡፡ ይህም በእጅ አዙር የማህበረሰብን ጤና ወደተሻለ ደረጃ እንደሚያደርሰው ሀሳቡን የደገፉት ተቋማትና ግለሰቦች ተናግረዋል፡፡  

ህጉን ያረቀቁት ተወካይ ኒኮል ዊልያምስ ይህ አዲስ ህግ ትምህርት ቤቶች ማሽኖቹን እንዲተክሉ እንደማያስገድድ ተናግረዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ በርካቶች ድጋፋቸውንና ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን ድጋፋቸውን ከሰጡት መኃል የሜሪላንድ  ጤና ቢሮ ሴክረተሪ ዶክተር ሎራ ሄሬራ ስካት ይገኙበታል፡፡ ዶ/ር ሎራ በጽሁፍ በሰጡት የድጋፍ ደብዳቤ እንዳስቀመጡት በቬንዲንግ ማሽን ኮንዶምና መሰል የወሊድ መቆጣጠሪያን ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ተደራሽ ማድረግ የተማሪዎችን ወሲባዊ ህይወት እንደማያበራክተውና ይልቅስ በተለይ ለአባላዘር በሽታዎች ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉ ተማሪዎችን ጤና እንደሚጠብቅ በጥናት እንደታየ ምስክርነታቸውን ሰተዋል፡፡  

ይህን ረቂቅ ህግ በመቃወም የቀረቡት የራይት ቱ ላይፍ ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ላውራ ቦግሊ ደሞ ይህን ህግ በመሻር ከኪንደርጋርተን ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ለአላስፈላጊ የጽንስ ማስወረጃ መድሃኒቶች ማጋለጥ እንደሆነና በግብር የተሰበሰበን ገንዘብ አላስፈላጊ በሆነ ጉዳይ ማባከን ነው ሲሉ በተቃውሞ ጽሁፋቸው ተናግረዋል፡፡ አክለውም ለአካለመጠን ካልደረሱ ልጆችጋ የሚደረግ የግብረስጋ ግንኙነት ወንጀል እንደሆነና ይህ በሆነበት ሁኔታ ለታዳጊዎች የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሐኒቶችን ማቅረብ ሳይሆን የሚያስፈልጋቸው የታላላቆች ምክርና ቁጥጥር እንደሆነ እንዲሁም ታዳጊዎች አዕምሯዊም ሆነ ስሜታዊ ብቃቱ ስለሌላቸው ራሳቸው በጤና ጉዳዮቻቸው ላይ እንዲወስኑ የሚያስችላቸው ብቃት የላቸውም ብለዋል፡፡  

ይህ ህግ አሁን ከተሻረ ቀጥሎ ደሞ የሚያስገድድ ህግ ይመጣል ስለዚህ ይህ ማሻሻያ ተግባራዊ መሆን የለበትም ያሉ ሲሆን አክለውም በርካታ ለጤና ጎጂ የሆኑ የወሊድ መቆጣጠሪያ ወይንም የጽንስ ማጨናገፊያ መድሓኒቶችን ለታዳጊዎች ተደራሽ በማድረግ ጤናቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዲፈጠር ሊያደርግ እንደሚችል አልፎ ተርፎም ትምህርት ቤቶችና አስተማሪዎች በተማሪዎች ላይ የደረሱ ወሲባዊ ጥቃቶችን ማጋለጥ ሲገባቸው ወደ መደባበቅ ሊያስገባቸው እንደሚችልና በዚህና በመሳሰሉት እንደሚቃወሙት ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጲክ ባልደረቦች በዲሲና በቨርጂንያ ያሉ ተመሳሳይ ህጎችን ለማየት የሞከሩ ሲሆን በዲሲም ሆነ በቨርጂንያ ኮንዶምን በቬንዲንግ ማሽን መሸጥ የሚከለክል ህግ እንደሌለና ትምህርት ቤቶች መሸጥ ከፈለጉ ከልካይ እንደሌለባቸው ተረድተዋል፡፡ 

መሉውን የድጋፍና የተቃውሞ ዝርዝር ይህንን ሊንክ ተከትለው ያገኙታል፡፡ 

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.