ከቨር (4)

Image: from Gemini

የሜሪላንድ ስቴት ፖሊስ እንዳሳወቀው ዛሬ ቅዳሜ ፌብሯሪ 22 ከሰዓት ከ4pm በፊት ባለአንድ ሞተር ሴስና አውሮፕላን ባጋጠመው የሀይል መቋረጥ ችግር ምክንያት በመኪና መንገድ ላይ ለማረፍ እንደተገደደ ታውቋል።

በአውሮፕላኑ ላይ አብራሪው ብቻ ሲሆን የነበረው ይኸው አብራሪም የ18 አመት ወጣት እንደሆነና ከአደጋው በኋላ በፕሪንስ ጆርጅ በሚገኝ የህክምና ተቋም ለህክምና እንደተወሰደ ፖሊስ አስታውቋል።

በዚህ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት በአን አረንደል ካውንቲ የሚገኙት ሾርሀም ቢችና ትራይተን ቢች መስቀለኛ መንገድ ለትራፊክ ዝግ ሆኖ ነው የዋለው። አደጋውን ለማጣራት የፌደራል ትራንስፖርቴሽን ደህንነት ቦርድና የፌደራል አቪዬሽን ባለስልጣን በቦታው የተገኙ ሲሆን ከምሽት 6፡30 ጀምሮ መንገዱ በአንድ በኩል ብቻ ተከፍቶ እንዲያገለግል ተደርጓል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.