ከቨር (3)

የሜሪላንድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ትላንት ሐሙስ ፌብሯሪ 20 ባወጣው መግለጫ I-895 ወይም የባልቲሞር ሀርበር ተነል ከሰኞ ፌብሯሪ 24 ጀምሮ እስከ ረቡዕ ፌብሯሪ 26 በመንገዱ ላይ በሚደረጉ እድሳቶች ምክንያት ወደ ሰሜን የሚወስደው የተነሉ መንገድ እንደሚዘጋና ወደደቡብ የሚወስደው መንገድ ወደ ላይም ወደ ታችም የሚሄዱ መኪኖች እንደሚያስተናግድ ይህን ተከትሎም የትራፊክ መስተጓጎል እንደሚኖር ተነግሯል። የመንገድ እድሳቱ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ከምሽት 9pm እስከ ንጋት 3am ይከናወናል።
ከሐሙስ ፌብሯሪ 27 ጀምሮ ደሞ በተቃራኒ ወገን ያለው ወደ ደቡብ የሚወስደው መንገድ ላይ በሚኖር ዕድሳት ሳቢያ እንዲሁ ከምሽት 9pm እስከ ንጋት 3am መንገዱ ይዘጋል። በተቃራኒ ወገን ያለው ወደ ሰሜን የሚወስደው የመንገዱ ክፍል እንዲሁ በሁለቱም ወገን ለሚሄዱ መኪኖች አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል። አሽከርካሪዎች ይህን ከግምት አስገብተው እንዲያሽከረክሩና አዳዲስ የፍጥነት ወሰኖች እንዲያስተውሉ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.