
የዲሲ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በ ኤክስ ገፃቸው እንዳሰፈሩት በዲሲ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 3 የሜሪላንድ አሽከርካሪዎችን ከሰዋል:: እኚህ 3 አሽከርካሪዎች በጋራ ከ90 ሺህ ዶላር በላይ የትራፊክ ቅጣት በአመታት ጊዜ አጠራቅመዋል::
ባለፈው አመት በዲሲ የፀደቀው ህግ የዲሲ መንግስት ከክልሉ ውጭ ያሉ አሽከርካሪዎች ላይ መክሰስ የሚያስችለው ስልጣን ሰቶታል:: በወቅቱ ኢትዮጲክ ስለ ህጉ የሰራችውን ዘገባ ለማየት ይህንይጫኑ::
