
የአይ አር ኤስ የበጎ ፈቃደኛ ታክስ አዘጋጆች (Volunteer Income Tax Assistance (VITA)ና Tax Counseling for the Elderly (TCE)) ከ60 አመት በላይ በመላው አሜሪካ ለሚገኙና የፕሮግራም መመዘኛውን ለሚያሟሉ ታክስ ከፋዮች የነጻ ታክስ አገልግሎት ሲያቀርብ ቆይቷል።
ዘንድሮም አመታዊ ገቢያቸው ከ67ሺህ ዶላር በታች የሆኑ ሰዎች የአይ አር ኤስ በጎ ፈቃደኞች ባዘጋጁትና በየአመቱ በሚዘጋጀው የነጻ የታክስ አገልግሎት መጠቀም ይችላሉ፡፡
ይህ የበጎ ፈቃደኞች ማህበር ታዲያ ዘንድሮም በየካውንቲውና ዲስትሪክቱ ይህንኑ ነፃ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግና መመዘኛውን ለሚያሟሉ ታክስ ከፋዮች የ2023 ታክሳቸውን ፋይል እንዲያደርጉ ለማገዝ በጎ ፈቃደኞችን አሰባስቦ ስራ እንደጀመረ ተነግሯል። በዚህ ፕሮግራም ለመጠቀም የተፈቀደላቸው
- አመታዊ ገቢያቸው 67,000$ ና ከዚያ በታች የሆኑ
- የአካል ጉዳት ያለባቸውና
- በእንግሊዝኛ ቋንቋ መግባባት የሚቸገሩ ታክስ ከፋዮች ሲሆኑ በተጨማሪም እድሜያቸው 60 አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ለአዛውንቶች በተዘጋጀ ተመሳሳይ ፕሮግራም መሳተፍ እንደሚችሉ ትገልጿል።
በዚህ ፕሮግራም በበጎ ፈቃደኝነት የሚያገለግሉ ታክስ ከፋዮች በሙሉ የአይ አር ኤስ ሙሉ ፍቃድ ያላቸውና መመዘኛውን ወስደው ያለፉ ባለሞያዎች ሲሆኑ አይ አር ኤስም ፕሮግራሙን በበላይነት ይቆጣጠረዋል። አብዛኞዎቹ ይህን አገልግሎት የሚሰጡ አገልጋዮች በቀጠሮ የሚሰሩ በመሆኑ መንገድ ከመጀመርዎ በፊት ደውለው ቀጠሮ ማስያዝ እንዳይረሱ። በዚህ ፕሮግራም ታክስዎን ሊያሰሩ ከፈለጉ የሚከተሉትን ዶክመንቶች ይዘው መሄድ ይኖርብዎታል።
Original photo identification for you and your spouse (if married filing jointly), such as a:
- Valid U.S driver’s license
- Employer ID
- School ID
- State ID (U.S.)
- Military ID
- National ID
- Visa
- Passport
Social Security cards for you, your spouse and dependents
- Note: If you need to request a replacement card or update your Social Security record, go to Social Security number & card to find the best way to do this.
An Individual Taxpayer Identification Number (ITIN) notice CP-01A, We assigned you an identity protection personal identification number (IP PIN) for you, your spouse and your dependents if you do not have a Social Security number (SSN)
- Proof of foreign status, if applying for an ITIN
- Birth dates for you, your spouse and dependents on the tax return
- Wage and earning statements (Form W-2, W-2G, 1099-R, 1099-MISC) from all employers
- Social Security Benefit Statements (SSA-1099), if applicable
- Interest and dividend statements from banks (Forms 1099)
- A copy of last year’s federal and state returns, if available
- Proof of bank account routing and account numbers for direct deposit, such as a blank check
- Total paid for daycare provider and the daycare provider’s tax identifying number, such as their SSN or business EIN
- Health Insurance Exemption Certificate, if received
- Forms 1095-A, Health Insurance Marketplace Statement
- Copies of income transcripts from IRS and state, if applicable
- To file taxes electronically on a married-filing-joint tax return, both spouses must be present to sign the required forms
በአቅራቢያችሁ ያለን የነፃ ታክስ ማዘጋጃ ቦታ ለማወቅ ይህን ሊንክ ተጭነው የዚፕ ኮድዎትን ያስገቡና FIND የሚለውን ይጫኑ፡