@ethiopique202(1)

ትላንት ረቡዕ ማርች 19 ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ በዲሲ ዳርቻ በሚገኙ የሜሪላንድ ከተሞች ካውንቲዎች ያሉ አሽከርካሪዎች በተበላሹ መንገዶች፤ በትራፊክ መጨናነቅ፤ እንዲሁም ባልተሟሉ የደህንነት ጉዳዮች ምክንያት በአመት እስከ 3500 ዶላር ድረስ ኪሳራ እንደሚያጋጥማቸው ትሪፕ የተባለ አገር አቀፍ የትራንስፖርት ጉዳዮች አጥኚ ድርጅት አስታውቋል፡፡ በጥናቱ እንደታየው አሽከርካሪዎችን ለዚህ ከፍተኛ ኪሳራ ያበቃቸው ከፍተኛ የሆነ የመኪና ጥገና ወጪ በተለይም የመኪና መንገዶች ጥራትና ደረጃቸው አነስተኛ በመሆኑና በየቦታው ያሉ ጉድጓዶችን በዋና ምክኛትነት ያስቀምጣሉ፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው የሚስተዋለው የትራፊክ መጨናነቅ ለአላስፈላጊ የጋዝ ወጪ እንደሚዳርግና ያለአግባብ የሚጠፋም ጊዜ በተመኑ ውስጥ ተካቷል፡፡ ሌላው ቀላል ቦታ ያልተሰጠው አሽከርካሪዎች በአደጋ ምክንያት የሚያጡት የገንዘብ መጠን ነው፡፡ 

እንደ ጥናቱ ከሆነ በዲሲ አካባቢ ባሉ የሜሪላንድ ከተሞችና ካውንቲዎች ካሉት መንገዶች 52 ከመቶ የሚሆኑት ከጥራት በታች እንደሆኑና በአማካይ አንድን አሽከርካሪ እስከ 788 ዶላር ለሚደርስ ወጪ እንደሚዳርጉ ተጠቁሟል፡፡ በተጨማሪም አንድ አሽከርካሪ (አማካይ አሽከርካሪ በአመት ከ12ሺ እስከ 15ሺ ማይል ይነዳል) በአማካይ 86 ሰዓት (የ2 ሳምንት ስራ እንደማለት ነው) የተዘጋጋ ትራፊክ በመጠበቅ ያሳልፋል ይህም አንድን አሽከርካሪ በአመት እስከ 2183 ዶላር ያከስረዋል፡፡

እንደ ኡበርና ሊፍት ያሉ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡና ቀኑን ሙ ሉ መኪና የሚያሽከረክሩ ሰዎች ደሞ ከአማካዩ ሰው በብዙ እጥፍ በነዚህ ምክኛቶች ለኪሳራ ሊዳረጉ እንደሚችሉ ይገመታል፡፡

ሙሉ ጥናቱን ለማየት ይህን ሊንክ ይጫኑ 

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.