
ፕሬዘደንት ትራምፕ ዛሬ ማርች 20 በፈረሙት ኤክሲኪውቲቭ ኦርደር አማካኝነት የዲፓርትመንት ኦፍ ኤጁኬሽን እንዲፈርስ አዘዋል፡፡ የዲፓርትመንት ኦፍ ኤጁኬሽንን እንዲያስተዳድሩ የመረጧቸውን የቀድሞ የሬስሊንግ ውድድር ተቋም አለቃ የሆኑት ማክማሆንንም የመጨረሻዋ የዲፓርትመንቱ አስተዳዳሪ እንደሆኑ አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዘደንት ትራምፕ በመግለጫው ላይ ከዚህ በኋላ ስቴቶች በትምህርት ጉዳይ ላይ አለቃ ናችሁ ብለዋል፡፡ ይህ ውሳኔ በተለይም ከዲ ኢ አይጋ ተደምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለስደተኛ ልጆች ይደረግ የነበረው የገንዘብና ሌሎች የአይነት ድጋፍ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል ተብሎ ይሰጋል፡፡