@ethiopique202 (18)

ቤት ለመግዛት የሚመረጠውን የስፕሪንግ ወራትን ተንተርሶ እንዲሁም የፌደራል መንግስት ሰራተኞች መፈናቀልን በማስመልከት በዲሲና አካባቢው የሚሸጡ ቤቶች ቁጥር ከአምና ተመሳሳይ ጊዜ አንጻር በ56% እንዳሻቀበ ተነግሯል።


ከአሮጌ ቤቶች በተጨማሪም አዳዲስ የተገነቡ ቤቶች ቁጥር እንደጨመረና ተደማምሮ ለሽያጭ ገበያ ላይ የቀረቡ ቤቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመራቸው የሪልተር ዶት ኮም መረጃ ጠቁሟል።

በአገር አቀፍ ደረጃ የሞርጌጅ መጠን ጃንዋሪ ላይ ከነበረው 7.25% ወደ 6.82% እንደወረደም ተነግሯል።


የሪልተር ዶት ኮም ቺፍ ኢኮኖሚስት የሆኑት ዳኒዬል ሄል እንደተናገሩት “የፌደራል መንግስት ሰራተኞች በአብዛኛው በሚገኙበት የዲሲ አካባቢ በርካታ ቤቶች ወደገበያ ለሽያጭ ወተዋል። ዋጋቸውም ከወትሮው በጥቂቱ ዝቅ ያለ ነው። ሆኖም የፌደራል መንግስት አካሄድ በግልጽ ስላልታወቀ ሁኔታው በማንኛውም ጊዜ ሊቀየር ይችላል። ምንም እንኳ በርካታ የቀድሞ የመንግስት ሰራተኞች እዚሁ አካባቢ ስራ በመፈለግ ባሉበት ቢቆዩም የተወሰኑት ግን ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደሌላ ቦታ ሊሄዱ ይችላሉ” ብለዋል።


በዚህ ደረጃ የሚደረግ ሰዎችን ከስራ የማፈናቀል ሂደት የቤት ገበያው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው እንደሚገመትና በርካታ ሻጮች በአካባቢው መኖራቸው እንዲሁም የዛን ያህል ገዢዎች አለመኖር የቤት ዋጋ እንዲወድቅ ሊያደርግ እንደሚችል ጠቁመዋል

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.