@ethiopique202 (21)

እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ከመጣን በኋላ ከምናስተውላቸው ነገሮች አንዱ የወቅቶች መፈራረቅ ነው። እዚህ እንደ አገር ቤት በዝናብና በጸሐይብ ብቻ ሸውደን አናልፍም አንዱ ወቅት ከሌላው ከፍተኛ የሆነ ልዩነት አለው። ከወቅቶች ሁሉ ደሞ ስፕሪንግ (ፀደይ) ሲመጣ ዲሲና አካባቢው ከወትሮ በተለየ ውበትና ድምቀት ይስተዋልባቸዋል። በርካታ በቀለማት ያሸበረቁ ፌስቲቫሎችም ይካሄዳሉ።

በዲሲና አካባቢው ደሞ ባህላዊ የሆነውን የቼሪ ብሎሰም ወቅትና ተያያዥ ፕሮግራሞች በጉጉት የሚጠበቁ ናቸው። በዚህ በዚህ የዲ ኤም ቪ አካባቢ ነዋሪ መሆን በራሱ የሚሰጠው ጥቅም አለ። በቀጣይ ቀናትም ዲሲና አካባቢው በርካታ ፕሮግራሞች አሉ። ከረጅሙና ቀዝቃዛው የክረምት ወቅት በኋላ በቼሪ አበቦች፤ በሙዚቃ፤ በተለያዩ የምግብና መጠጥ መዛኛዎች፤ መጫወቻዎችና የመሳሰሉ ፕሮግራሞች ይደምቃል። እኛም የተወሰኑትን እንዲህ ዘርዝረናቸዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ አመታዊው ብሔራዊ የቼሪ ብሎሰም ፌስቲቫል ቅዳሜ ማርች 22 በዋርነር ቲያትር ተመርቆ ይከፈታል። ይህ ፕሮግራም በአሜሪካና በጃፓን መኃከል ያለውን ወዳጅነት የሚገለጽበት ፕሮግራም ነው። በዚህ ፕሮግራም ላይ በአካል መገኘት ለማይችሉ ፕሮግራሙ በቀጥታ ይተላለፋል።

በተጨማሪም በዲሲ ያሉ ምግብ ቤቶችና ድርጅቶች በቼሪ ብሎሰም የተዋጁ ምግቦች፤ መጠጦችና ሌሎች መዝናኛዎችን አዘጋጅተዋል

ረጋ ያለ ፕሮግራም ከፈለጉ ደሞ የዋይት ኃውስን ውስጣዊ ገጽታ የሚያዩበት ዘ ፒፕልስ ሀውስ የተባለው ሙዚየም ከዋይት ኃውስ አንድ ብሎክ ላይ በ1700 Pennsylvania Avenue ሰዎች በነጻ ገብተው የሚዝናኑበትና ስለዋይት ኃውስ የሚማሩበት ፕሮግራም አለው።

የቼሪ ብሎሰም ዋና መናኸሪያ በሆነው ታይዳል ቤዚን አቅራቢያ የእንኳን ደህና መጣችሁ የሚሏችሁ ባለሞያዎችና የፕሮግራሞቹ ባለቤቶች እስከ ኤፕሪል 6 ይኖራሉ። በዚህ ቦታ ላይም የተለያዩ የመዝናኛና የመማማሪያ ፕሮግራሞች ይኖራል።

ከሁሉም በላይ የምንጓጓለት ፕሮግራም ለኛም ለልጆቻችንም የብሎሰም ካይት ፌስቲቫል ነው። ይህ አመታዊ የካይት ፕሮግራም በመጪው ቅዳሜ ማርች 29 ከ10am ጀምሮ በናሽናል ሞል ሜዳ ላይ ይከናወናል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.