
ምክትል ፕሬዘደንት ጄዲ ቫንስ ወደ ስልጣን ሲወጡ ለ2 አመት ያህል ጊዜ በመኖሪያ ቤትነት ሲገለገሉበት የነበረውን ቤት ለገበያ አቅርበውት ነበር።
በፌብሯሪ 2023 ጄዲ ቫንስና ባለቤታቸው ኡሻ ቫንስ ይህንን ቤት በ1.639 ዶላር እንደገዙት የህዝብ መዛግብት ያሳያሉ።
ታዲያ ከሰሞኑ በዚሎው ላይ እንደታየው ምክትል ፕሬዘደንትና ባለቤታቸው ኡሻ ቫንስ ቤታቸውን በ1 ሚልየን ስምንት መቶ ስልሳሰባት ሺህ ሃያ አምስት ዶላር በመሸጥ የ228 ሺ ዶላር ትርፍ አግኝተዋል።
ይህ ቤት በ2530 ስኩዌር ፊት ላይ ያረፈ ሲሆን ባለ አምስት መኝታቤትና 4 መታጠቢያ ቤት አለው።