
የቨርጂንያ ገቨርነር እንዳስታወቁት በስቴቱ ጸድቆ ከነበረው በጀት ላይ የ900 ሚልየን ዶላር ቅነሳ እንዳደረጉና ይህም ሊሆን የቻለው የፌደራል መንግስት የገንዘብ ፖሊሲ አስመልክቶ በቨርጂንያ የሚሰበሰበው ግብር ሊቀንስ እንደሚችል መተንበዩን ተከትሎ እንደሆነ ተነግሯል።
ይህ የበጀት ቅነሳም በዋናነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካፒታል ፕሮጀክቶችን ግንባታ አቋርጧል። ከነዚህም ዋነኞቹ የቨርጂንያን የቴክኖሎጂ ባለሞያዎች ቁጥር ለማሳደግ አስቦ የነበረውን የቨርጂንያ ቴክ ኢኖቬሽን ካምፓስ በአሌክሳንድርያ ግንባታ እንዲቆም ምክንያት ሆኗል።
በተመሳሳይ በቨርጂንያ የአልደርማን ቤተመጻህፍትን ለማዘመን የነበረው እቅድ የሚስተጓጎል ሲሆን እንደ ጆርጅ ሜሰን ያሉ ተቋማት ደሞ ተቸማሪ ተማሪዎችን ለመያዝ የሚያስችል አዲስ ግንባታና የአሮጌዎቹ ህንጻዎች እድሳት እንዲሁ ሊስተጓጎል እንደሚችል ተጠቁሟል።
ከነዚህም በተጨማሪ በመንግስና በግሉ ሴክተር በተጓዳኝ ይሰጡ የነበሩ የህጻናት ክብካቤ ላይም ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሏል።