@ethiopique202 (20)

ሜይ 14, 2025፦  የክልሎችን የክሬዲት ስኮር የሚተምነው ሙዲ የተባለው ተቋም የስቴቱን አጠቃላይ የክሬዲት ቦንድ ደረጃ ወደ Aa1 ዝቅ አደረገ። ይህ የደረጃ ዝቅጠት የመጣው የክልሉ የረጅም ጊዜ የፊስካል ጤንነት መጓደሉን እና የፌዴራል ፖሊሲ ለውጦች የክልሉን ተጋላጭነት እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ነው።

ሞዲ ከጠቀሳቸው ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ የሜሪላንድ በጀት ላይ የ$3.3 ቢሊዮን ዶላር ጉድለት በመምጣቱና ይህም የስቴቱን ኢኮኖሚ ይጎዳል ተብሎ በመታሰቡ ነው። ለዚህ የበጀት ጉድለት ምላሽ ለመስጠትና ክፍተቱን ለመሙላት በሚልም የሜሪላንድ ሕግ አውጪዎች $1.6 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት አዲስ የታክስ ጭማሪዎችና ሌሎች የገቢ ማግኛ ዘዴዎችን ለ2026 አሳልፈዋል፡፡ ይህ ሁሉ ጥረት ቢደረጉም፣ የደረጃ አሰጣጥ ኤጀንሲው የሜሪላንድ የበጀት አወቃቀር ዘላቂነት እና የወደፊት ገቢ ግዴታዎችን ለመወጣት በቂ ስለመሆኑ ጥርጣሬውን በመግለጽ ከ52 አመታት በሁዋላ የሜሪላንድን የክሬዲት ውጤት ዝቅ አድርጎታል፡፡ 

ገዥው ዌስ ሙር እና ሌሎች የዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪዎች የቅርብ ጊዜ የፌዴራል ውሳኔዎች የክልሉን የፋይናንስ አቋም እንዳዳከሙ ተናግረዋል። በዋሽንግተን የሥራ ቅነሳ፣ የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ እና የፖሊሲ ለውጦች በፌዴራል የሥራ ስምሪት እና ኮንትራቶች ላይ በእጅጉ ጥገኛ በሆነው በሜሪላንድ ኢኮኖሚ ላይ ተጨማሪ ጫና ፈጥረዋል ብለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪዎች በክልል ደረጃ የተወሰዱ ውሳኔዎችን ተጠያቂ አድርገዋል። የሃውስ አናሳ ፓርቲ ጅራፍ ጄሲ ፒፒ የዴሞክራት ፓርቲ ሕግ አውጪዎችአ አስፈጻሚዎች ለዓመታት የፈጸሙትን ብልሹ የፋይናንስ  አሠራር ሲተቹ ከመጠን ያለፈ ወጪ እና የአመራሮች አርቆ ያለማሰብ ለደረጃው ዝቅጠት ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

የክሬዲት ስኮር (ደረጃው) መውረድ ሜሪላንድ ለመሰረተ ልማት ግንባታና ለመሳሰሉት ወጪዎች ብድር ለመበደር ቦንድ ስታወጣ ከፍተኛ የወለድ ፐርሰንት እንደምትጠየቅና ይህም የስቴቱን ኢኮኖሚ እንደሚጎዳው ተነግሯል፡፡ ክልሉ ለመንገድ ጥገና፣ ለትምህርት ቤት ግንባታ ወይም ለመሠረተ ልማት ጥገና ለመሳሰሉት የሕዝብ ፕሮጀክቶች ገንዘብ ለመበደር ከወትሮው የበለጠ መክፈል ሊኖርበት ይችላል ማለት ነው። የደረጃው ዝቅጠት እንቅፋት ቢሆንም፣ ሙዲ የሜሪላንድን የወደፊት ዕይታ ከ”አሉታዊ” ወደ “የተረጋጋ” ቀይሯል፣ ይህም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተጨማሪ የደረጃ ዝቅጠት እንደማይጠበቅ ያመለክታል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.