@ethiopique202-2-1

በአሌክሳንድርያ ከተማ ይህዝብ ትምህርት ቤቶች ባሉ የከፍተኛ ሁለተና ደረጃ ተማሪዎች ለሚማሩ ጥቁር ተማሪዎች ተለይቶ በተዘጋጀው በዚህ የስኮላርሺፕ ዕድል ላይ የ2025 አሸናፊዎች ጌዲየንና መሰረት እንደሆኑ ታውቋል፡፡  በ1800ዎቹ መጨረሻ በአሌክሳንድሪያ ተገርፈውና ተደብድበው ለህልፈት በተዳረጉ ሁለት ጥቁር ታዳጊዎች መታሰቢያነት የሚሰጠውን የ2025 ጆሴፍ ማኮይ እና ቤንጃሚን ቶማስ መታሰቢያ የትምህርት ዕርዳታን ጨምሮ ሁለት ከአሌክሳንድሪያ ሲቲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመረቁ ተማሪዎች ተመርጠዋል።

ለውድድሩ አዘጋጆች ስለ ሽልማቱ ሀሳባቸውን ሲያካፍሉም መሰረት ስለሽልማቱ አመስግና በቀጣይም 2 አመት የሚፈጀውን የጥርስ ንጽህና ትምህርቷን ለመከታተል በሰሜን ቨርጂኒያ ኮሚኒቲ ኮሌጅ ለመማር እንዳቀደችና ይህ የገንዘብ ድጋፍም ይህን ጥረቷን እንደሚያግዝ አስታውቃለች። 

ጊዲዮንም እንዲሁ የጆሴፍ ማኮይ የትምህርት ስኮላርሺፕተሸልሟል። እሱም እንደ መሰረት በሰሜን ቨርጂኒያ ኮሚኒቲ ኮሌጅ የፖለቲካ ሳይንስ ለመማር እና በሕዝብ አገልግሎት ሥራ ለመሰማራት አቅዷል። ይህ የትምህርት ስኮላርሺፕ በየአመቱ 3000 ዶላር ለትምህርታቸው በመክፈል በአራት ዓመታት ውስጥ በአጠቃላይ እስከ $12,000 ዶላር ድጋፍ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡ የዚህ ስኮላርሺፕ የሽልማት ፕሮግራም በመጪው ሳምንት ሜይ 22 2025 ይከናወናል፡፡

እ.ኤ.አ. 2023 ጀምሮ የአሌክሳንድሪያ የሕዝብ መታሰቢያ ፕሮጀክት ለእነዚህ የትምህርት ዕርዳታዎች ከ$43,000 ዶላር በላይ ሰብስቧል። ኢትዮጲክ ለሁለቱም ተማሪዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ትላለች፡፡ 

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.