12/12/2024
Screen-Shot-2022-05-08-at-14.13.50


ማንኛውም የዲሲ አዛውንት በዚህ የትራንስፖርት ኮስት-ሺውሪንግ ፕሮግራም ማመልከትና ከተፈቀደለት የድጎማው ተጠቃሚ መሆን ይችላል። ይህ ኮኔክተር ካርድ የቪዛ ዴቢት ካርድ ሲሆን የተፈቀደላቸው ሰዎች ካርዱ በፖስታ መኖሪያቸው ድረስ ይላካል። ይህን የቪዛ ካርድ እንዳሻዎ ከፈለጉ ለሜትሮ ባስና ባቡር ካልሆነ ለኡበርና ሊፍት ወይንም ለካፒታል ባይክሼር መጠቀም ይችላሉ።
በፕሮግራሙ መሳተፍ የሚፈልጉ ከፈለጉ በአካል፤ ወይም በፖስታ ወይንም ኦንላየን ማመልከት ይችላሉ። የተፈቀደላቸው አዛውንቶች በወር እንደ ገቢያቸው እስከ $100 ወደ ቪዛ ካርዳቸው ይላክላቸዋል። ይህንን ካርድም ቢያንስ በወር ሶስት ጊዜ መጠቀም ይኖርባቸዋል። ካልተጠቀሙበት ዲአክቲቬት ይደረጋል። በተጨማሪም ካርዱን ከትራንስፖርት ውጪ ለሆነ አገልግሎት ከተጠቀሙ ዲአክቲቬት ይደረጋል። ለማመልከት ይህን ሊንክ ይጫኑና ወደማመልከቻው ይሂዱ.. https://bit.ly/የአዛውንቶችትራንስፖርት
ፕሪንት ማድረግ የምትችሉት የወረቀት ማመልከቻ ከፈለጋችሁ በፌስቡክ ሜሴንጀር ጠይቁን። .pdf ፋይሉን 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ እንልካለን። ማመልከቻውን እንድናግዛችሁ ከፈለጋችሁም እንዲሁ በፌስቡክ ሜሴንጀር አናግሩን።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት