ከፌርፋክስ ካውንቲ መንግስት ድረ-ገፅ ላይ እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ ይህ WORKFORCE INNOVATION AND OPPORTUNITY ACT የተባለ ፕሮግራም የስራ ፈላጊዎችንና ቀጣሪዎችን ፍላጎት ለማሟላት ተብሎ የተዘጋጅ የአዋቂዎች ፕሮግራም ነው።
ማንኛውም እድሜው ለስራ የደረሰ ሰው በዚህ ፕሮግራም ታቅፎ ለተለያዩ ስራዎች ብቁ የሚያደርጉትን ስልጠናዎች መውሰድ ይችላል።
» » ፕሮግራሙ ከሚያቀርባቸው አገልግሎቶች በከፊል
» » የስራ ስልጠና በተለይም በጣም ተፈላጊ በሆኑ ሙያዎች
» » የስራ መፈለግ ድጋፍ፤ ሲቪ/ሬዙሜ አፃፃፍ ድጋፍና ለስራ ቅጥር ኢንተርቪው ድጋፍ
» » አስፈላጊ የሙያ ስልጠናዎችና ሰርተፊኬቶች
» » ደሞዝ የሚከፈልባቸው የስራ ልምድ ማግኛ ፕሮግራሞች
» » ለስራ የሚያስፈልጉ አልባሳት፤ ዩኒፎርሞች፤ ማሽኖች እና የመሳሰሉ ማሟላት ይገኝበታል
ለበለጠ መረጃ ይህን ቪዲዮ መመልከት ይችላሉ።
በተጨማሪ በየሳምንቱ አርብ ጧት 10፡00 እና ከሰዓት 2፡00 ላይ የመረጃ ኦሪየንቴሽን/ኢንፎ ሴሽን አለ። ለመመዝገብ ሊንኮቹን ተከትለው ይሂዱ።
በተጨማሪም ይህ ፕሮግራም እድሜያቸው ከ17-24 ለሆኑ ወጣቶች የተለየ ፕሮግራም አለው። ሊንኩን ተጭነው ማየት ይችላሉ።