የሞንጎምሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ከጁን 27-30፡ 2022 ከጠዋት 8 a.m. እስከ 2 p.m. የተማሪ አውቶቡስ ሾፌሮች የስራ ቅጥር ምልመላ ያካሄዳል። በቀጥታ በአካል ለሚቀርቡ አመልካቾች ቃለ-መጠይቅ የሚካሄድበት አድራሻ፦ Shady Grove Transportation Depot፣ 16651 Crabbs Branch Way in Rockville ነው።
የአውቶቡስ ሹፌር ለመሆን መሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች፦
- ቢያንስ 21 አመት ዕድሜ ያለው/ያላት።
- በመንጃ ፍቃድ ላይ ግድፈት ከአንድ ነጥብ ያልበለጠ ንጹህ የአሽከርካሪነት ሪኮርድ
- ቢያንስ የሶስት አመት የመንዳት ልምድ እና በ U.S. ቢያንስ አንድ አመት የመንዳት ልምድ ያለው/ያላት
- ሁሉንም የቅድመ-አገልግሎት ስልጠና እና የፈተና መስፈርቶችን የማሟላት ችሎታ
- ህጋዊ የሜሪላንድ ደረጃ C መንጃ ፍቃድ፣ CDL ወይም የ CDL ፍቃድ ያለው/ያላት
ለቃለ መጠይቅ ለመዘጋጀት፦
የስራ ልምድዎን (resume) ቅጂ ይዘው ይምጡ።
MCPS Careers portal ላይ አጭር መገለጫ ይጻፉ። የሞንጎምሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች እጩዎችን ኦንላይን በማመልከት ሊረዳቸው ይችላል። ለማመልከት የሚያስፈልግዎት የኢሜል አድራሻ ብቻ ነው።
ጥያቄዎች ካሉዎት 240-740-6080 ይደውሉ።