የአርሊንግተን ቨርጂንያ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ የ73 ዓመት አዛውንት የሆኑት ወይዘሮ አቦነሽ ባሳለፍነው እሁድ ኦገስት 27 2023 ዓም ታስረው በነበረበት የአርሊንግተን ካውንቲ እስር ቤት እንዳረፉ አስታውቋል።
ፖሊሶች ወይዘሮ አቦነሽን ጧት 7፡02 am ላይ ሲያገኟቸው ምንም ምላሽ ባለማግኘታቸው ነብሳቸውን ለማዳን ጥረት አድርገው እንደነበርና በኋላም 7፡10 ላይ የድንገተኛ አደጋ ተከላካዮች ተመሳሳይ ጥረት አድርገው ነበር። ወይዘሮ አቦነሽ ምንም መሻሻል ባለማሳየታቸው ወደሆስፒታል የተወሰዱ ቦሆንም ነፍሳቸውን ማዳን እንዳልተቻለ ገልጸዋል።
ወይዘሮ አቦነሽ ኦገስት 13 2023 ዓም በፖሊስ የዲሲ ኤርፖርትን ጥሰው በመግባት ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ሲሆን ወደ ላውደን ካውንቲ እስር ቤት ለመሄድ ቀን እየተጠባበቁ ነበር። ወይዘዎ አቦነሽ የጎዳና ተዳዳሪ እንደነበሩና በተደጋጋሚ ወደ ኤርፖርቶች በመግባት ያስቸግሩ እንደነበር ተገልጿል።
የአርሊንግተን ካውንቲ ፖሊስ ለቤተሰቦቻቸው እንዳረዳና የሞታቸውን መንስዔ እያጣራ እንደሆነም አሳውቋል።
የወይዘሮ አቦነሽን ህልፈት ተከትሎም የጥቁሮች መብት ተከላካይ የሆነው የናሽናል አሶሴሽን ኦፍ አድቫንስመንት ኦፍ ከለርድ ፒፕል መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫውም በቨርጂንያ እስር ቤቶች በተለየ ሁኔታ በጥቁሮች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እንዳሳሰበው የተቋሙ የአርሊንግተን ቅርንጫፍ ፕሬዘደንት የሆኑት ማይክል ሄሚንገር ተናግረዋል።
ስለዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ በርካታ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘትና የኢትዮጲክ ዲጂታል ጋዜጣ በኢሜይልዎ እንዲደርስዎት ይህን ሊንክ ተጭነው ይመዝገቡ
ለዲሲ የአመቱ ምርጥ በጎ ፈቃድ ጥቆማ መስጠት ተጀመረ
የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር ማህበረሰባቸውን በበጎ ፍቃድ በማገልገል ላቅ ያለ ሚና ተጫውተዋል ለሚሏቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ዕውቅናና ሽልማት ለማበርከት እንዳቀዱ ዛሬ አሳውቀዋል። ነዋሪዎች ይህ ሽልማት ይገባቸዋል የሚባሉ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን እንዲጠቁሙም ጥሪ አቅርበዋል። እናንተም እኛን ኢትዮጲክን ጨምሮ ሌሎች ይገባቸዋል፤ የበጎ ፍቃድ አገልግሎታቸው አርኪ ነው የምትሏቸውን ግለሰቦች ወይንም ተቋማት ካሉ ከስር ባለው ሊንክ ገብታችሁ ጥቆማችሁን ማስገባት ትችላላችሁ።