የአርሊንግተን ነዋሪ የሆነው ዋሲሁን ወልደአማኑኤል በፌብሯሪ 20 በገዛው የፒክ _4 ሎተሪ የ200 ሺህ ብር አሸናፊ ሆኗል፡፡ የፒክ_4 ሎተሪ አንዱ ቲኬት የ5ሺ ዶላር ሽልማት ያለው እድለኛው ቁጥር ደሞ 4 4 4 4 ነበር፡፡ አቶ ዋሲሁን ታዲያ ይሕን 4 4 4 4 የሆነ የሎተሪ ቲኬት አርባ ፍሬ በመግዛቱ በእያንዳንዱ 5000 ታስቦ 200ሺ ዶላር አሸናፊ ሆኗል፡፡
ዋሲሁን 30ውን ሎተሪ አርሊንግተን 2901-11 South Glebe Road ከሚገኘው ጃያንት አስሩን ደሞ 3903 Mount Vernon Avenue in Alexandria ከሚገኘው ታይገር ማርኬትና ቤከሪ እንደገዛ የቨርጂንያ ሎተሪ ዜና ያሳያል፡፡