በዲሲና አካባቢው በተለይም በፌርፋክስ ካውንቲና በላውደን ካውንቲ ቨርጂኛ አካባቢዎች ዛሬ ማምሻውን ድንገት በሚከሰት ሀይለኛ ንፋስ እንደሚኖርና ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል የብሄራዊ አየር ንብረት አገልግሎት ዛሬ ረቡዕ ኖቨምበር 20 ባወጣው ማስጠንቀቂያ አሳወቀ፡፡ እንደማስጠንቀቂያው ከሆነ ከምሽት 8pm እስከ 11pm ድረስ ባለው ጊዜ ከ35 እስከ 45 ማይል በሰዐት የሚምዘገዘግ ንፋስ ሊኖር እንደሚችልና በአንዳንድ አካባቢዎች ይህ ንፋስ እስከ 50 ማይል በሰዐት ሊጓዝ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
ይህ ንፋስ ከቤት ውጪ ያሉና በአግባቡ ያልተቀመጡ ቁሶችን አንከባሎ የመውሰድ አቅም ሊኖረው እንደሚችል ተነግሯል፡፡ ይህን ተከትሎም ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተመክሯል፡፡ ይህ የንፋስ ውዥንብር ለሊቱን ከስሞ እንደሚያድርም መግለጫው አብሮ ጠቁሟል፡፡
በዚህ ወቅት የወደቀ የመብራት ወይንም የስልክ ገመድ ካዩ በ911 ለፖሊስ በአፋጣኝ ይደውሉና ያሳውቁ፡፡