
ኢትዮጲክ በየአመቱ የሚያደርገው የታክስ ባለሞያዎች ውድድር ዘንድሮም ተመልሶ መቷል። ባለፈው ዓመት ባደረግነውና 139 ሰዎች በተሳተፉበት መጠይቅ አንባቢዎች በጠቅላላው 16 ባለሞያዎችን የጠቆሙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ደሞ በ 36% አንደኛ የነበረው ሬሜዲ ታክስ ነበር። ደንበኞች ምርጫቸውን የሚሰጡባቸው መስፈርቶች የባለሞያው ዕውቀት፤ የደንበኛ አያያዝ፤ የስራ ቅልጥፍናና የመሳሰሉት እንደሆኑም ነግረውን ነበር።

ዘንድሮስ የእርስዎ ምርጫ ማን ነው? ከስር ያለውን ፎርም በመሙላት ወይም መጨረሻ ላይ ያስቀመጥነውን በተን በመጫን ምርጫዎን ያሳውቁን።
ከላይ ያለው ፎርም ካልሰራልዎት ይህን ተጭነው መልስዎን ይስጡን። እናመሰግናለን።