495

የ495 ኤክስፕረስ መንገዶች ማስፋፊያ ፕሮጀክት አንዱ አካል በሆነውና 495 ኔክስት ተብሎ በሚጠራው በዚህ ፕሮጀክት ሊሰራ ለታቀደው የኤክስፕረስ ሌን መግቢያ መንገድ አቃፊ የሆኑ 295 ጫማ ርዝመት ያላቸው ድልድይ ደጋፊ ብረቶችን ወደሰሜን በሚሄደው የደለስ ኮሪደር ኢንተርቼንጅ ላይ ባለው የ I-495 መንገድ ላይ ይተክላሉ።

ይህ ግንባታ የሚከናወነው የደለስ አየር ማረፊያ መገንጠያ ባለበት የ495 መንገድ ላይ ሲሆን ይህም ፕሮጀክት ከነገ ከአርብ ጃንዋሪ 24 ጀምሮ እስከ ጃንዋሪ 27 ድረስ ይህ በከፊል ተዘግቶ እንዲቆይ ያስገድዳል።
ይህን ተከትሎም ለወትሮው 6 መስመር (2 የኤክስፕረስና 4 መደበኛ መስመሮች) የነበረው ይህ መንገድ ግንባታው እስኪያልቅ በሁለቱ የኤክስፕረስ መስመሮች (ሌን) ብቻ ለ1 ማይል ያህል አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።

ይህም የትራፊክ መስተጓጎሉንና መጨናነቁን እስከ ሜሪላንድ ድረስ ሊያደርሰው እንደሚችል ተተንብዩዋል። ይህን ተከትሎ ከሚፈጠሩ መስተጓጎሎች ለመጠበቅም አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የቨርጂንያ ትራንስፖርት ቢሮ አሳስቧል።

Courtesy: VDOT

ይህ የትራፊክ መስተጓጎል ከአርብ ጃንዋሪ 24 9pm ላይ የሚጀምር ሲሆን። ሁሉም ግንባታዎች ተጠናቀው መንገዶቹ በድጋሚ ሙሉ ለሙሉ ክፍት የሚሆኑት ሰኞ ጃንዋሪ 27 ንጋት 5am ላይ ነው ተብሏል

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.